የቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያን በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ
የበጀት አመት 2022 (FY22)
በFY22፣ የግዛት የትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ቢሮ (OSSE) እና AidKit በቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያ አማካኝነት ለ3,217 የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች $38,372,000 አከፋፍለዋል። ብቁ የሆኑ የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች በሰራተኛ አይነታቸው (ለምሳሌ፣ መምህር፣ ረዳት መምህር፣ የቤት ውስጥ ተንከባካቢ፣ ወዘተ) እና በቅጥር ሁኔታቸው (ለምሳሌ፣ የሙሉ ጊዜ ወይም የትርፍ ጊዜ) ላይ በመመስረት ለአንድ ጊዜ ክፍያዎች እስከ $14,000 ድረስ ተቀብለዋል።
ለቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያ የFY22 ማመልከቻ በኦገስት 15፣ 2022 የተከፈተ ሲሆን ሴፕቴምበር 20፣ 2022 5 p.m. ላይ ተዘግቷል። AidKit ማመልከቻውን አቅርቧል፣ የገንዘብ ድጋፎችን ሰጥቷል እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ አድርጓል።
የFY22 መርጃዎች
FY23
በ FY23፣ OSSE እና AidKit በቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያ አማካኝነት ለ4,085 የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች $41,908,750 አከፋፍለዋል። ብቁ የሆኑ የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች በሰራተኛ አይነታቸው እና በቅጥር ሁኔታቸው ላይ በመመስረት በኦክቶበር 2022 እና በሴፕቴምበር 2023 መካከል እያንዳንዳቸው $3,500 የሚደርሱ እስከ አራት ክፍያዎች ተቀብለዋል።
ለቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያ የFY23 ማመልከቻ ኖቬምበር 1፣ 2022 የተከፈተ ሲሆን ኦገስት 15፣ 2023 በ5 p.m. ላይ ተዘግቷል። በFY22 በAidKit በኩል ተጨማሪ ክፍያ የተቀበሉ እና በOSSE ፈቃድ በተሰጠው የልጅ እድገት ተቋም ውስጥ በብቁ የሰራተኛ አይነት ውስጥ ተቀጣሪ እንደሆኑ የቆዩ የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች በ FY23 ተጨማሪ ክፍያዎችን ለማግኘት ተጨማሪ ማመልከቻዎችን ማስገባት አይጠበቅባቸውም።
የ FY23 መርጃዎች
- ያልተፈቀደ ክፍያ ፖሊሲ
- ብቁነት፣ የክፍያ ፖሊሲ እና የስርጭት መርሃ ግብር
- ብቁ ያለመሆን ይግባኞች ፖሊሲ እና ሂደት
- በተደጋጋሚ የተጠየቁ ጥያቄዎች
- ምናባዊ የመረጃ ክፍለ ጊዜ
ተያያዥ ይዘቶች፦