Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

osse

Office of the State Superintendent of Education
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የፈቃድ አሰጣጥ እና ትግበራ

በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የሚሰሩ ሁሉም የልጅ እንክብካቤ ፕሮግራሞች የተቀመጡትን የልጅ እንክብካቤ መስፈርቶችን ማክበር አለባቸው። የልጅ እንክብካቤ መስፈርቶች ፕሮግራሞች በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ያለውን ዝቅተኛ የእንክብካቤ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። ፕሮግራሞች ከፍተኛ የትግበራ ደረጃ መጠበቅ አለባቸው። በፕሮግራሙ የትግበራ ታሪክ ውስጥ የሚካተቱ የልጅ እንክብካቤ መስፈርቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፣

  • ባለቤትነት፣ አደረጃጀት፣ እና አስተዳደር
  • የልጆች ቁጥጥር
  • የመሳሪያዎች እና እቃዎች አቋም
  • የሥነምግባር ልምዶች
  • የልጅ/ሠራተኛ ተመጣጣኝነት
  • የውስጥ እና የውጭ አካባቢዎች
  • የሠራተኛ ብቃት እና የስልጠና እድገት
  • የወንጀል የኋላ ታሪክ ማጣሪያዎች
  • የምግብ ዝርዝር(ሜኑ) እና የቀረቡ ምግቦች

በተጨማሪ፣ የልጅ እድገት ተቋማት ፈቃድ ለማግኘት በሌሎች የዲስትሪክት ኤጀንሲዎች የሚያስፈልጉ የንጽህና፣ የህንጻ እና የእሳት አደጋ ህጎችን እና የሊድ ክሊራንሶችን ማክበር ይጠበቅባቸዋል። እነዚህም የይዞታ ሰርተፊኬት፣ የመኖሪያ ቤት ፈቃድ፣ የሊድ ክሊራንስ፣ የእሳት አደጋ ፈቃድ፣ ከተዋሃዱ(ኢንኮርፖሬትድ ከሆነ) የጥሩ አቋም ደብዳቤ እና በ12 ተከታታይ ወራት ውስጥ በOSSE ውስጥ የልጅ እንክብካቤ ኦሪየንቴሽን(ገልጻ) ላይ የተሳትፎ የምስክር ወረቀትን ያካትታሉ።

በግልጽ ቀሪ ካልተደረገ በስተቀር፣ እያንዳንዱ ተንከባካቢ እና የልጅ እድገት ተቋም፣ ምድቡ ምንም ይሁን በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የልጅ እንክብካቤ ተቋምን ለማካሄድ ፈቃድ ሊኖረው ይገባል።

ከታች ያሉትን ማንኛውንም ነጻ የሚያደርጉ መስፈርቶችን ካላሟሉ፣ ለፈቃድ ማመልከት ይኖርብዎታል። ነጻ የሚያደርጉ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፣

  • የልጅ ጠባቂ ቤት ወይም የአንድ ቤተሰብ የልጅ ቤት ውስጥ አልፎ አልፎ ልጅን መጠበቅ፤
  • ለተንከባካቢ በልጁ ቤተሰብ ክፍያ እየተከፈለ በልጅ ቤት ውስጥ የሚሰጥ እንክብካቤ
  • በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እንደተገለጸው፣ የልጅ ሞግዚት በመጋራት(ናኒ ሼር)ከአንድ በላይ ለሆኑ ልጆች የሚሰጥ እንክብካቤ፤
  • መደበኛ ያልሆነ ወይም አልፎ አልፎ በወላጆች ቁጥጥር የሚደረጉ የልጆች የጨዋታ ቡድን፤
  • አባላት አገልግሎቶችን መጠቀም እንዲችሉ ጊዜያዊ የልጅ እንክብካቤን እንደ ጥቅማ ጥቅም የሚያቀርቡ የአዋቂ ጂሞች ወይም ክለቦች፤
  • ወላጅ(ጆች) በተመሳሳይ ካምፓስ ውስጥ ከሚማር ወይም የትምህርት ፕሮግራም ከሚከታተል ልጅ ጋር የአዋቂ ትምህርት ፕሮግራሞችን በሚከታተሉበት ወቅት በጊዜያዊነት ለተወሰነ ጊዜ የልጅ እንክብካቤ አገልግሎቶችን በሚያቀርቡበት ጊዜ፤
  • ልጅን ማዕከል ያደረጉ የንግድ ሥራዎች ማስጠናት፣ ሙዚቃ፣ ዳንስ፣ ስፖርት፣ ወይም አርትን ጨምሮ ሌሎች ሴሽኖችን፣ ክፍሎችን ወይም እንቅስቃሴዎችን ወላጅ(ጆች) ወይም ሞግዚት(ቶች) የንግድ ሥራው በሚሰራበት ቅጥር ግቢ ውስጥ ባሉበት የሚሰጡ፤
  • በሃይማኖታዊ አገልግሎቶች ወቅት በአምልኮ ቦታዎች ላይ የሚሰጥ እንክብካቤ፤
  • ዝምድና ባለው ሰው የሚሰጥ እንክብካቤ፤
  • በፌዴራል መንግሥት ንብረት ላይ በፌዴራል መንግሥት የሚተዳደሩ ተቋሞች፣ ነገር ግን በፌዴራል መንግሥት ንብረት ውስጥ ወይም ቦታ ላይ ቦታ የሚጠቀም የግል አካል የፌደራል ህግ በግልጽ ከኮሎምቢያ ዲስትሪክት የቁጥጥር ስልጣን ነጻ ካላደረገው በስተቀር ከግዴታው ነጻ አይደለም፤
  • ከቅድመ መዋዕለ ህጻናት-መዋዕለ ህጻናት 3 ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ለተማሪዎች የሙሉ ቀን ትምህርት አገልግሎት የሚሰጡ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የህዝብ ትምህርት ቤት ወይም የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት፤
  • ከቅድመ መዋዕለ ህጻናት-መዋዕለ ህጻናት 3 ጀምሮ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል 12 ድረስ ተማሪዎች የሙሉ ቀን ትምህርት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ትምህርት ቤት፤
  • በመዋዕለ ህጻናት ህግ መሠረት የመዋዕለ ህጻናት የትምህርት አገልግሎቶችን በመዋዕለ ህጻናት እድሜ ክልል ላሉ ልጆች የሚሰጡ በOSSE የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው ማህበረሰባዊ መሠረት ያላቸው ተቋማት፤
  • ለትምህርት ቤት ለደረሱ ልጆች የቅድመ ትምህርት ቤት እንክብካቤ ብቻ፣ የድህረ ትምህርት ቤት እንክብካቤ ብቻ፣ ወይም የበጋ ካምፕ ብቻ የሚሰጡ ተቋማት።

ፈቃድ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

ማዕከል

የቤት

የፈቃድ አሰጣጥ ኦሪየንቴሽን(ገለጻ)

የእድሳት ማመልከቻ ፓኬት

ከማዕከል/ቤት/ትምህርት ቤት ውጭ ጊዜ

ማዕከል

የቤት

ከትምህርት ቤት ውጭ ጊዜ

ቅሬታዎች እና ያልተለመደ ሁኔታን ሪፖርት ማድረግ

በልጆች የእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ያለን ቅሬታ ወይም ያልተለመደ ሁኔታ እንዴት ሪፖርት ማድረግ እችላለሁ?

የልጆች የእንክብካቤ አገልግሎቶች ላይ ቅሬታ ለማቅረብ የአቤቱታ የስልክ መስመር ጋር በ (202) 727-2993 ይደውሉ ወይም ኢሜይል ይላኩ ለ [email protected]። በተጨማሪ አቤቱታዎችን ለፈቃድ አሰጣጥ እና አተገባበር ክፍል በ (202) 727-7295 ፋክስ ማድረግ ይቻላል።

የፈቃድ አሰጣጥ የምርመራ ግምገማ መጠየቅ

ከግዴታ ቀሪ ለመደረግ ጥያቄ

የግለሰቡ አድራሻ፣

(202) 727-1839

የግለሰቡ ፋክስ፣

(202) 741-5403

የግለሰቡ TTY፣

711

የግለሰቡ የወለል #:

ስድስተኛ ፎቅ

የሥራ ሰዓቶች፣

ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከጥዋት 8:30 እስከ 5 ከሰዓት

የአገልግሎት ስፍራ፣

የGIS አድራሻ፣

1050 First Street, NE

ከተማ፣

ዋሺንግተን

ክልል፣

ዲሲ

ዚፕ፥

20002

ተያያዥ ይዘቶች፣

የልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት

 

 

Contact Phone: 
(202) 727-1839
Contact Fax: 
(202) 741-5403
Contact TTY: 
711
Contact Suite #: 
Sixth Floor
Office Hours: 
Monday to Friday, 8:30 a.m. to 5 p.m.
Service Location: 

1050 First Street, NE

GIS Address: 
1050 First Street, NE
City: 
Washington
State: 
DC
Zip: 
20002