Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

osse

Office of the State Superintendent of Education
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት

ሶስት ዓይነት የልጅ እንክብካቤ ፕሮግራሞች አሉ፣

  • የልጅ እድገት ማዕከላት፣
  • የቤተሰብ የልጅ እንክብካቤ ቤቶች ተብለው በተጨማሪ የሚታወቁ የልጅ እድገት ቤቶች፣ በአቅራቢው ቤት ውስጥ ቁጥራቸው እስከ 6 የሚደርሱ ልጆችን የሚንከባከቡ፤ እና
  • ሰፊ የልጅ እድገት ቤቶች፣ ቁጥራቸው እስከ 12 የሚደርሱ ልጆችን የሚንከባከቡ።

በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ያሉ አብዛኛው የልጅ የእንክብካቤ ፕሮግራሞች ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል። (ከግዴታው ነጻ የሆኑ የተወሰኑ አሉ። ይህ ፈቃድ የማያስፈልጋቸው የፕሮግራሞችዝርዝር ነው።

የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት

ለመጀመሪያ ጊዜ ፈቃድ ለማግኘት፣ የልጅ እንክባካቤ አቅራቢ በሚከተለው ሂደት ውስጥ ማለፍ አለበት፤

1. አቅራቢው የልጅ የእድገት ማዕከል ወይም የቤት ፈቃድ ኦሪየንቴሽን(ገለጻውን) መውሰድ አለበት። የልጅ እንክብካቤ ፈቃድ ለማግኘት ከማመልከት በፊት ኦሪየንቴሽኑን(ገልጻውን) በአካል ወይም በኦንላይን የፈቃድ ዌቢናር አማካኝነት ማጠናቀቅ ግዴታ ነው።

2. ከማመልከቻዎ ጋር የሰርተፊኬት ቅጂ መግባት አለበት። ሰርተፊኬቶች የሚሰጡት ሴሽኑን(ክፍለ ጊዜውን) ላጠናቀቁ ግለሰቦች ብቻ ነው። አስፈላጊውን ኦሪየንቴሽን(ገለጻ) ሳያጠናቅቁ ማመልከቻውን ማስገባት ይህ መስፈርት እስኪሟላ ድረስ የማመልከቻውን ሂደት ማገድን ሊያስከትል ይችላል። ስለ ፈቃድ አሰጣጥ ማመልከቻ እና መስፈርቶች የበለጠ ለመማር፣ የልጅ የእድገት ማዕከል ኦሪየንቴሽን(ገለጻ) [PDF] ወይም የልጅ እድገት የቤት ኦሪየንቴሽን(ገለጻ) [PDF] ይመልከቱ።

3. አቅራቢው ቦታ ይመርጥ እና የይዞታ ሰርተፊኬት ወይም የቤት የይዞታ ፈቃድ ከተጠቃሚ እና የቁጥጥር ጉዳዮች ዲፓርትመንት(DCRA)፣ የህንጻ እና የመሬት ቁጥጥር አስተዳደር፣ ዞኒንግ ክፍል ያገኛል፣ ይህም የሚገኘው 1100 Fourth St. SW, Second Floor ላይ ነው። የይዞታ ሰርተፊኬትዎ ወይም የቤት ይዞታ ፈቃድ የሚከተለውን መረጃ ማካተት አለበት፤ እርስዎ የልጅ እንክብካቤ ማዕከሉን፣ እንክብካቤ የሚደረግላቸው ከፍተኛ የጨቅላ ህጻናት እና ልጆች ቁጥር፣ የሥራ ሰዓት፣ እና የሠራተኛ ብዛትን ማመልከት አለብዎ።

4. አቅራቢው በአካል ወይም በኦንላይን የፈቃድ አሰጣጥ ዌቢናር አማካኝነት የፈቃድ አሰጣጥ ኦሪየንቴሽን (ገለጻ)ን ማጠናቀቅ አለበት፣ ይህም ተጓዳኝ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ማለፍን ይጨምራል። የፈቃድ አሰጣጥ ኦሪየንቴሽን(ገልጻ) ማመልከቻ እንዴት ማስገባት እንደሚቻል መረጃ እና መመሪያዎችን ይሰጣል።

5. አቅራቢው የሚከተሉትን አግባብነት ያላቸውን ቅጾችን ለቀደመ ትምህርት፣ የፈቃድ አሰጣጥ እና ትግበራ ክፍል ዲቭዥን (LCU) ያቀርባል፣

  • የልጅ የእድገት ማዕከል ማመልከቻ፣ የማመልከቻ ክፍያ $75፣ እና ሁሉም አግባብነት ያላቸው ቅጾች የሚከተሉትን ጨምሮ(ይመልከቱ 5 DCMR 103.4, 103.5, 108.2)፣
  • አመልካች የወንጀል የኋላ ታሪክ ማጣሪያዎች እና የልጅ እድገት ምዝገባ ማጣሪያዎችን ማሟላቱን የሚያሳይ ሰነድ
  • የክሊን ሃንድስ አክት ማረጋገጫ (ማመልከቻው ከገባበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ)
  • የተንከባካቢ ብቃቶች (ማመልከቻው በገባበት ወቅት ተቀጥሮ ከነበር)
  • ተመጣጣኝ ሽፋን ያለው የመድን ማረጋገጫ (ማለትም፣ አጠቃላይ የንግድ ሀላፊነት፣ umbrella “Follow Form”(መድንዎ ከሚሸፍነው በላይ ያለውን ሀላፊነት የሚሸፍን ዋስትና)፣ የጾታዊ ጥቃት እና ትንኮሳ ሀላፊነት፣ እና የተሽከርካሪ ሀላፊነት)
  • የእሳት አደጋ የደህንነት ምርመራ ማረጋገጫ ከዲሲ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ የህክምና አገልግሎቶች (FEMS)
  • የሊድ ቀለም ሰርተፊኬት ወይም ከኢነርጂ እና አካባቢ ዲፓርትመንት የክሊራንስ ሪፖርት
  • በሰነድ አረጋጋጭ ፊት የተደረገ የህንጻ አጠቃቀም ስምምነት (አግባብ ከሆነ)
  • ደህንነቱ የተጠበቀ የመውጫ ቦታ የተቋም መዘጋትን ከሚያሳይ የፈቃድ መግለጫ ጋር (አግባብ ከሆነ)
  • የተዋሃዱ(ኢንኮሮፖሬትድ) ከሆኑ ወይም ለመዋሃድ እቅድ ካሎት፣ ከDCRA, Corporation Division at 1100 Fourth Street, SW, ሁለተኛ ፎቅ የሚሰጠውን.የጥሩ አቋም ሰርተፊኬት ዋናውን(ለ30 ቀናት የጸና) ማቅረብ አለብዎ።

6. የፈቃድ ሰጭ ስፔሺያሊስት አቅራቢውን ያገኛል፣ የመጀመሪያ ምርመራ የሚደረግባቸውን ተግባራትን ይጠቁማል፣ እና ለመጀመሪያ ምርመራ ቀጠሮ ይይዛል።

7. የፈቃድ ሰጪ ስፔሺያሊስት የልጅ የእድገት ማዕከል ወይም ቤቱን ይመረምራል። በምርመራ ጉብኝት ወቅት ምን እንደሚፈጠር ይወቁ

8. የፈቃድ ሰጪው ስፔሻሊስት በጉብኝቱ ወቅት ያልተከበሩ ነገሮች መኖራቸውን ከወሰነ፣ የጉድለት መግለጫ (SOD) ይሰጣል።

9. በምርመራው ወቅት የተገለጹ ሁሉም ጉድለቶች በምርመራው ወቅት በተሰጠው የጉድለት መግለጫ(SOD) ላይ በተሰጠው የጊዜ ማዕቀፍ ውስጥ መስተካከል/መቀነስ አለባቸው።

10. የፈቃድ ሰጭው ስፔሺያሊስት ሁሉም ጉድለቶች መስተካከላቸውን ለማረጋገጥ ቀጠሮ ያስይዝ እና ተከታይ ምርመራዎችን ያከናውናል። ይህ ከሆነ፣ አቅራቢው ምርመራውን ያልፋል።

11. የፈቃድ ሰጭዎ ስፔሺያሊስት እና የፕሮግራም ማኔጀር የመጨረሻ ጉብኝት ያካሂዳሉ። ይህ ጉብኝት የማረጋገጫ ጉብኝት ተብሎ ይጠራል።

12. አቅራቢው ፈቃድ ያገኛል። ፈቃዱ ለሶስት ዓመታት ያገለግላል እና በየሶስት ዓመት መታደስ አለበት። የፈቃድ አሰጣጥ የፍሰት ሂደት ይመልከቱ [PDF]።

የፈቃድ እድሳት ሂደት

የልጅ እንክብካቤ ፈቃዶች በየሶስት ዓመት መታደስ አለባቸው። ፈቃድ የማደስ ሂደቱ አዲስ ፈቃድ ለማግኘት ካለው ሂደት ጋር በጣም ይመሳሰላል።

1. አቅራቢው የእድሳት ማመልከቻ፣ ክፍያ፣ እና አግባብነት ያላቸውን ሁሉንም ቅጾች ነባሩ ፈቃድ አገልግሎቱ ከሚያበቃበት 90 ቀን በፊት ማቅረብ አለበት። T

አቅራቢው የሚከተሉትን አግባብ ያላቸውን ቅጾች ማቅረብ አለብት፣

  • የቀድሞ የወንጀል የኋላ ታሪክ ማጣሪያዎችን የመስክ አሻራ እና የልጅ
  • የጥበቃ ምዝገባ ማጣሪያዎችን በማድረግ አመልካች ማጠናቀቁን የሚያሳይ ሰነድ።
  • የክሊን ሃንድስ አክት ማረጋገጫ (ማመልከቻው ከገባበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ)
  • ተመጣጣኝ ሽፋን ያለው የመድን ማረጋገጫ (ማለትም፣ አጠቃላይ የንግድ ሀላፊነት፣ umbrella “Follow Form”(መድንዎ ከሚሸፍነው በላይ ያለውን ሀላፊነት የሚሸፍን ዋስትና)፣ የጾታዊ ጥቃት እና ትንኮሳ ሀላፊነት፣ እና የተሽከርካሪ ሀላፊነት)
  • የእሳት አደጋ ምርመራ ማረጋገጫ ከዲሲ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ የህክምና አገልግሎቶች (FEMS)
  • በሰነድ አረጋጋጭ የተመዘገበ የህንጻ አጠቃቀም ስምምነት ከአስፈላጊው ሰነድ ጋር (ይመልከቱ 5A DCMR 103.5 (g))፣ አግባብ ከሆነ
  • ደህንነቱ የተጠበቀ የመውጫ ቦታ የተቋም መዘጋትን ከሚያሳይ የፈቃድ መግለጫ ጋር (አግባብ ከሆነ)

2. ማመልከቻው እና አግባብነት ያላቸውን ሁሉም ቅጾች ለቀደመ ትምህርት፣ የፈቃድ አሰጣጥ እና ትግበራ ክፍል ዲቭዥን (LCU) ቀርቧል።

3. የፈቃድ ሰጭ ስፔሺያሊስቱ አቅራቢውን ያገኛል፣ ለእድሳት ምርመራ የሚደረግባቸውን ተግባራትን ይጠቁማል፣ እና የእድሳት ምርመራ ቀጠሮ ይይዛል። 

4. የፈቃድ ሰጪ ስፔሺያሊስት የልጅ የእድገት ማዕከል ወይም ቤቱን ይመረምራል። የፈቃድ ሰጪው ስፔሻሊስት በጉብኝቱ ወቅት ያልተከበሩ ነገሮች መኖራቸውን ከወሰነ፣ የጉድለት መግለጫ (SOD) ይሰጣል። በምርመራው ወቅት የተገለጹ ሁሉም ጉድለቶች በምርመራው ወቅት በተሰጠው የጉድለት መግለጫ(SOD) ላይ በተሰጠው የጊዜ ማዕቀፍ ውስጥ መስተካከል/መቀነስ አለባቸው።

5. የፈቃድ ሰጭው ስፔሺያሊስት ሁሉም ጉድለቶች መስተካከላቸውን ለማረጋገጥ ቀጠሮ ያስይዝ እና ተከታይ ምርመራዎችን ያከናውናል። ይህ ከሆነ፣ አቅራቢው ምርመራውን ያልፋል።

6. አቅራቢው የታደሰውን ፈቃድ ያገኛል፣ ይህም ከተሰጠበት ቀን አንስቶ ለሶስት አመታት ያገለግላል።

የግለሰቡ TTY፣

711

ተያያዥ ይዘቶች፣

የቀደመ ትምህርት ደንቦች እና ፖሊሲዎች

Contact TTY: 
711