Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

osse

Office of the State Superintendent of Education
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የህጻን እንክብካቤ አቅራቢ የመቆጣጠሪያ እና የፍተሻ ሂደት

እያንዳንዱ ፈቃድ ያለው የልጅ እንክብካቤ አቅራቢ የፈቃድ እና የጤና እና የደህንነት መስፈርቶችን ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ የክትትል ጉብኝቶች ይደረግባቸዋል። እነዚህ ጉብኝቶች የሚካሄዱት በፈቃድ ሰጭ ስፔሺያሊስት ነው። አቅራቢዎች በየዓመቱ አንድ የታወቀ ጉብኝት እና አንድ ያልተጠበቀ ጉብኝት ይኖራቸዋል። ተጨማሪ ጉብኝቶች በማንኛውም ጊዜ ሊደረጉ ይችላሉ።

በእነዚህ ጉብኝቶች ወቅት፣ የፈቃድ ሰጭ ስፔሺያሊስቱ የሚከተሉትን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ነገሮችን ያጣራል፥

  • አስፈላጊ የሆኑት የሰራተኛ፣ ልጆች፣ እና ተቋም ሰነዶች መሟላታቸውን ያጣራል
  • አካባቢውን መፈተሽ። ይህ የሚሆነው ፈቃድ በሚሰጥበት ወቅት፣ ወይም ቦታው ሲቀየር ነው። ፍተሻውን(ምርመራውን) ለማለፍ የሚያስፈልጉት የሚከተሉት ናቸው፥
    • ከእድሜ ጋር ተመጣጣኝ የሆኑ አቅርቦቶች እና መሳሪያ (ለምሳሌ፣ የህጻን አልጋዎች፣ መጫወቻዎች፣ መጽሀፍት፣ እና ሌሎች እቃዎች)
    • በቂ የማስቀመጫ ቦታ
    • ሁሉም የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያዎች መሸፈን አለባቸው
    • የጽዳት እቃዎች ህጻናት የማይደርሱበት ቦታ ናቸው
    • የእጅ አስተጣጠብ ሂደቶች ተለጥፈዋል
    • በሁሉም የህጻን አልጋዎች መካከል የሁለት ጫማ ርቀት ቦታ መኖር

ከጉብኝቱ በኋላ፣ የፈቃድ ሰጪው ስፔሺያሊስት መረጃውን እና ሰነዶችን በፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ውስጥ ያስቀምጣል።

በጉብኝቱ ወቅት የፈቃድ ሰጭ ስፔሺያሊስቱ ችግሮችን ወይም ጥሰቶችን ካገኘ፣ እሱ ወይም እሷ መቀየር ወይም መሻሻል ያለባቸውን ዝርዝር ነገሮች ለአቅራቢው ይሰጣሉ። አቅራቢው ለውጦችን የሚያደርግበት የጊዜ ገደብ ይሰጠዋል፥

  • ለአዲስ ፈቃድ ማመልከቻ፥ 60 ቀናት
  • ለፈቃድ እድሳት ወይም ሌሎች ምርመራዎች፥ 30 ቀናት፣ ወይም ከዚያ ያነሰ ጊዜ በጣም ከባድ ለሆኑ ጥሰቶች

ጉብኝቱ የአዲስ ፈቃድ አካል ከሆነ፣ የመጨረሻ 'የማረጋገጫ ጉብኝት' አለ። ከዚያ፣ አቅራቢው ፈቃድ ያገኛል። ሙሉዉን የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት ይመልከቱ።

ተያያዥ ይዘቶች፥

የቀደመ ትምህርት ደንቦች እና ፖሊሲዎች