OSSE ለአስተማማኝ የዳታ ማስተላለፍ Boxን መጠቀም ሀሙስ፣ ፌብሪዋሪ 1፣ 2018 ላይ ተሸጋግሯል።
የዚህ ሰነድ አላማ
የዚህ ሰነድ አላማ ዳታን በአስተማማኝ ሁኔታ በሚተላለፍበት ወይም ከመንግስት የትምህርት ቢሮ ተቆጣጣሪ (OSSE) መረጃ በሚገኝበት ጊዜ የተማሪውን የግል ሚስጥር ለመጠበቅ መነሻ መምሪያ ለመስጠት ነው። ስለ ዳታ የግል ሚስጥርነት አጠቃላይ መነሻ በተጨማሪ፣ ይህ ሰነድ የተማሪን መረጃ ለብቻ ወይም በOSSE ያለው አስተማማኝ መድረክ ውጭ የሚፈጠር ተደጋጋሚ ያልሆነ የዳታ ማስተላለፍን በሚመለከት ልዩ መመሪያ ይሰጣል።
የግል ሚስጥራዊነት አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው? OSSE ለተማሪዎች እና ቤተሰቦች የላቀ ትምህርት ለመስጠት እና በDC ትምህርት እየተደረገ ያለውን እድገት ለማስጠበቅ፣እና ለማሳደግ ይተጋል። OSSE በእቅዱ ስትራቴጂክ እቅዱ ውስጥ ከአራት አስፈላጊ ቅድሚያዎች ውስጥ እንደ አንዱ ከፍተኛ ጥራት እና ተግባራዊ የሚደረጉ ዝርዝሮችን ለማቅረብ ቃል ገብቷል።
እንደ DC የመንግሥት ትምህርት ኤጄንሲ ፣ OSSE በቤተሰብ ትምህርታዊ መብቶች እና ግላዊ ሚስጥር (FERPA) በሚፈቀደው መሠረት ስለ ተማሪዎች እና ሕፃናትን ከየአካባቢው የትምህርት ኤጀንዲዎች (LEAs) ፣ ማህበረሰብ መሰረት ያደረጉ ድርጅቶችን ያካትታል (CBO) መረጃ ይቀበላል እና ያስተላልፋል። በእነዚህ ሁሉ አካላት የሰራተኞች መረጃ የእነሱን መረጃ ማግኘት ጥንቃቄ የተሞላበት መመሪያዎችን የመጠበቅ አስፈላጊ ሀላፊነት አለበት ፣ መረጃውን ማግኘት የግል እና የተጠበቀም ነው።
በእነዚህ ሁሉ አካላት የሰራተኞች መረጃ የእነሱን መረጃ ማግኘት ጥንቃቄ የተሞላበት መመሪያዎችን የመጠበቅ አስፈላጊ ሀላፊነት አለበት፣ መረጃውን ማግኘት የግል እና የተጠበቀም ነው።
በግል ሊለይ የሚችል መረጃ (PII) ምንድን ነው?
በግል ሊለይ የሚችል መረጃ (PII) መረጃ ማለት፣ ብቻውን ወይም በውህድ፣ ከአንድ የተለየ ተማሪ ጋር ሊገናኝ የሚችል፣ የሚከተሉትን የሚያካትት ነገር ግን ያልተወሰነ፣
- የተማሪ፣ ወላጆች፣ ወይም ሌላ የቤተሰብ አባሎች ስም።
- የተማሪ፣ ወላጆች፣ ወይም ሌላ የቤተሰብ አባሎች አድራሻ።
- የግል መለያ፣ እንደ የማህበራዊ ደህንነት ቁጥር፣ ልዩ የተማሪ መለያ (እንደ OSSE’s USI)፣ ወይም ባዮሜትሪክ ሪከርድ።
- ቀጥተኛ ያልሆኑ መለያዎች፣ እንደ የትውልድ ቀን፣ የትውልድ ቦታ፣ ወይም የእናት ስም።
አስተማማኝ የፋይል ማስተላለፊያ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
የተማሪ መረጃ የሚጠቀሙ ሁሉም ሰራተኞች ሃላፊነት በተሞላበት እና ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲይዙት የሃፊነት ሸክም አለባቸው። አስተማማኝ የፋይል ማስተላለፍ የተማሪን መረጃ ለመጠበቅ አንድ አስፈላጊ ዘዴ ነው።
PII ለማጋራት ኢሜይል የሚመረጥ መንገድ አይደለም ምክንያቱም ወደፊት በሚተላለፍ ወይም ሌላ ያለላኪው ፍቃድ የሚሰራጭ መልእክቶች በመሳሪያዎች፣ ኔትዎርኮች፣ ሰርቨሮች፣ እና የተቀባዩ መሳሪያ ሊጠለፍ ይችላል።
የOSSE Box እኔ ምን ማወቅ ያስፈልገኛል?
Box ምንድን ነው?
OSSE አስተማማኝ የዳታ ማስተላለፊያ ሲስተም Boxን ይይዛል፣ የዳታ ፋይሎች ኤሌክቶሮኒክ በሆነ መንገድ በOSSE እና ሌላ ኤጀንሲዎች እና እነሱን የሚያገለግሉ ድርጅቶች መካከል ሲዘዋወሩ የDC ተማሪዎችን PII ለመጠበቅ እንደ አንድ መንገድ ይጠቀመዋል። ይህ በOSSE ሰራተኛ እና የትምህርት ምክትል ከንቲባ ቢሮ(Deputy Mayor for Education, DME)፣ LEAs፣ የDC የህዝብ ትምህርት ቤቶች(DC Public Schools, DCPS)፣ የኮሎምቢያ ግዛት የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ቦርድ (Public Charter School Board, PCSB)፣ ትምህርት ቤቶች፣ CBOs፣ ገንዘብ ተቀባዮች እና ኮንትራክተሮች መካከል የዳታ መጋራትን ያካትታል።
Box ሌሎችን ጨምሮ ለDCPS፣ የህዝብ ቻርተር LEAs፣ PCSB፣ DME፣ እና የመጀመሪያ ትምህርት CBOs አቃፊዎች አሉት። የPII ማስተላለፍ የሚያስፈልጋቸው፣ የእያንዳንዱ እቃ አቃፊ ለተለየ ፕሮጀክቶች ወይም ተግባሮች በጣት የሚቆጠሩ ንኡስአቃፊዎችን ይይዛል። ለእነዚህ ፕሮጀክትን መሰረት ያደረጉ አቃፊዎች ግብዣዎች የሚሰጡት በግለሰብ ደረጃ ነው።
ገጹን የሚያስተዳድረው ማነው?
DAR ገጹን የሚያንቀሳቅሰው እና የሚጠብቀው ሃላፊነት ያለው ክፍል ነው።
Shenee Akinmolayan፣ የBox የOSSE አስተዳዳሪ፣ ለክፍሉ ገጹን ያስተዳድራሉ፣ የሚያካትተውም ለተጠቃሚዎች የፕሮጀክት አቃፊ ግብዣዎችን መላክ እና ሁሉም አቃፊዎች እና ወደ Box የግል መግቢያን ማዘጋጀት፣ መጠበቅ እና መሰረዝን ነው።
መግቢያ ማን ሊያገኝ ይችላል?
Box OSSE በመደበኛ ሁኔታ የሚያጋራቸው በቤተሰብ ትምህርታዊ መብቶች እና ግላዊ ሚስጥር (Family Educational Rights and Privacy Act, FERPA) የሚጠበቁ ዳታን የሚይዝ አቃፊዎች አሉት። ይህ የኮሎምቢያ ግዛት የአካባቢው የትምህርት ኤጀንዲዎች (local education agencies, LEAs) (የኮሎምቢያ ግዛት የህዝብ ትምህርት ቤቶች፣ ወይም DCPS፣ እና የህዝብ ቻርተር LEAs ሁለቱም)፣ የኮሎምቢያ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ቦርድ ( Public Charter School Board, PCSB)፣ እና ማህበረሰብ መሰረት ያደረጉ ድርጅቶችን ያካትታል። OSSE ለአቃፊዎች እና ማንኛውም ንኡስአቃፊዎች ፕሮጀክትን መሰረት ባደረገ መልኩ ፍቃዶች ይሰጣል። ሌላ ተጠቃሚዎች የሚያካትቱት ሁሉም ከOSSE ጋር በአስተማማኝ መልኩ የሚያስተላልፉ ሻጮች፣ ኤጀንሲዎች እና ግለሰቦችን ነው። ለተጠቃሚዎች ወደ ገጹ መግቢያ የሚሰጠው እንደየግለሰቡ ጉዳይ ሁኔታ ነው።
ፋይሎችን እንዴት መጫን ወይም ማውረድ እችላለሁ?
እባክዎ በ Box Quick Reference Guide (Box አጭር የማጣቀሻ መመሪያ) ላይ መረጃ ይመልከቱ።
ፋይሎቹ በገጹ ላይ ለምን ያክል ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ?
ገጹ ለመጫን ነው፣ ለማስቀመጥ አይደለም። ዳታ ፋይሎች እንደወረዱ ወዲያው እና ተፈላጊነታቸው እንዳበቃ መወገድ አለባቸው። ሁሉም ፋይሎች በBox ከ60 ቀናት በኋላ አውቶማቲክ በሆነ መልኩ እንዲወገዱ ሆነው ይዘጋጃሉ።
ፋይል ወደ ተሳሳተ አቃፊ ወይም የተሳሳተ ቦታ በስህተት ከተጫነ እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ?
ወደ ተሳሳተ አቃፊ ወይም የተሳሳተ ቦታ በስህተት የተጫነ ፋይል አግባብ ላልሆነ እይታ በተጨማሪ እንዳይጋለጥ ለመጠበቅ ወዲያውኑ መወገድ አለበት። ማንኛውም የOSSE ሰራተኛ እንዲህ ያለውን አግባብ ያልሆነ መጫን ያወቀ ወዲያውኑ የሚያስፈልጉትን ቀጣይ እርምጃዎች ላይ ድጋፍ ሊያደርጉ የሚችሉትን ለShenee Akinmolayanማሳወቅ አለበት።
ጥያቄዎች ካለኝ ማንን ማግኘት አለብኝ?
ወደ አስተማማኝ የመጫን ስፍራ መግቢያ ጥያቄዎች
Demetrius Brown, Management Analyst
Email: [email protected]
Phone: (202) 545-7243
ስለዚህ ፖሊሲ ጥያቄዎች፣
Gwen Rubinstein, Data Analysis Manager
Email: [email protected]
Phone: (202) 374-3723