Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

osse

Office of the State Superintendent of Education
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

Read about OSSE In Your Language: English  |  አማርኛ  |  中文  |  Français  |  한국어  |  Español  |  Tiếng Việt

This page contains information about the Office of the State Superintendent of Education for Amharic speakers.

ተልዕኮ

እንደ ግዛቱ የትምህርት ኤጀንሲ፣ ኦሲ (OSSE) የዲሲ ተማሪዎች መሻሻልን ለማስቀጠል፣ ለማፋጠን እና ለማጎልበት፣ ከትምህርት እና ሌሎች ተዛማጅ ስርዓቶች ጋር በጥምረት፣ በአስቸኳይ እና ዓላማ ባለው ሁኔታ መልኩ ይሰራል።

ራዕይ

ዲሲ የውጤት ክፍተትን ይዘጋል እና በሁሉም ዕድሜ እና ዳራ ላይ የሚገኙ ሰዎች በትምህርት ቤት ውስጥ እና በሕይወት ላይ መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል።

የኦ.ኤስ.ኤስ.ኢ ስራ ምንድን ነው?

የእስቴት የትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ጽ/ቤት (OSSE - ኦ.ኤስ.ኤስ.ኢ) ለዲሲ ነዋሪዎች የትምህርት ጥራትን የማሳደግ ኃላፊነት ያለበት የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የትምህርት ኤጀንሲ ነው። ኦ.ኤስ.ኤስ.ኢ ለአሜሩካ የትምህርት መምሪያ የዲስትሪክቱ ግንኙነት ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን የሚከተሉትን ቁልፍ ተግባራቶቹን ለማሳካት ከዲስትሪክቱ ባህላዊ እና የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ጋር በቅርበት ይሰራል፥

የተመረጡ አገልግሎቶች፥

የዲሲ የትምህርት ቤት ሪፖርት ካርድ

የ የዲሲ ትምህርት ቤት ሪፖርት ካርድ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ስለሚገኙት ሁሉም የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ላይ ቤተሰቦች እንዲመለከቱ ያደርጋል። የትምህርት ቤት ሪፖርት ካርድ ስለ አንድ ትምህርት ቤት ጠቅላላ መረጃ የሚያቀርብ መሳሪያ ነው፣ እና አንድ ትምህርት ቤት አፈፃጸሙ እንዴት እንደሆነ ወይም ምን ላይ መሻሻል እንደሚገባው ለማወቅ ያስችሎታል። ሁሉም ግዛቶች፣ ዲሲን ጨምሮ፣ እያንዳንዱ ተማሪ ስኬታማ መሆን አለበት አዋጅ [Every Student Succeeds Act ወይም ኢሳ (ESSA) በሚባለው ሕግ ለቤተሰብ የሚመቹ ሪፖርት ካርዶችን ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል። የሪፖርት ካርዶቹ በፌደራል ደረጃ የሚያስፈልጉ ሆነው ሳለ፣ የልጆቻቸው ትምህርት ቤት ላይ እንዲሳተፉ ለሚጠቀሙባቸው ቤተሰቦች እና ማህበረሰቡ ዓባለት ጠቃሚ ናቸው። ባለፈው ዓመት ላይ፣ የግዛቱ የበላይ ተቆጣጣሪ ትምህርት ቢሮ [Office of the State Superintendent of Education (OSSE)] የዚህን ሪፖርት ካርድ መዘጋጀት የሚመሩ 4,000 የወላጆች እና የማህበረሰብ ዓባልትን ድምጽ አዳምጧል።

መሪዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች ትምህርት ቤቶች እንዴት እየሰሩ እንዳለ የተለመዱ የእውነታ ማሳያ አሃዞችን በዲሲ ውስጥ ለእያንዳንዱ ሰው ለማሳየት ከሚሰጡት ተመሳሳይ ምንጭ ላይ የዲሲ ትምህርት ቤት ሪፖርት ካርድ ከፍተኛ ጥራት ያለው መረጃ ይወስዳል። የዲሲ ትምህርት ቤት ሪፖርት ካርድ የትምህት ቤት ግልጽነት ዘገባ [School Transparency and Reporting (STAR)] መዋቅር እና የትምህርት መርሀግብር አወጣጥ እና ከትምህርት ውጪ የሚሰጡ አገልግሎቶች፣ የትምህርት ውጤት፣ የትምህርት ቤት ከባቢ እና ተጨማሪ ነገሮች ውስጥ ያሉ የስታር (STAR) ብዙ የመረጃ ነጥቦችን ጨምሮ ከ 150 በላይ የመረጃ ዓባልትን ይይዛል።

ስለ ዲሲ ትምህርት ቤት ሪፖርት ካርድ የበለጠ ለማወቅ ከታች ያንብቡ ወይም DCSchoolReportCard.org ላይ ይሂዱ"

የእንግሊዘኛ ተማሪ [English Learner (EL)] መርሀግብር

"በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በፌደራል ሕግ መሰረት የእንግሊዘኛ ተማሪዎች (ELs) የእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቃታቸውን እንዲያጎለብቱ እና እንደ አቻ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ተወላጆች የሚጠበቅባቸውን ተመሳሳይ የትምህርት ፈተና እንዲቋቋሙ ማድረግ አለባቸው።

በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሕዝብ (District of Columbia Public) ወይም የሕዝብ ቻርተር (Public Charter) ትምህርት ቤት ውስጥ ከመመዝገብ በኋላ፣ ልጁ/ጅቷ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቃት እንዳለው/ላት ለመወሰን ሁሉም ወላጆች/አሳዳጊዎች በቤት ውስጥ የሚሞላ የቋንቋ ዳሰሳ ጥናት (Home Language Survey) መሙላት አለባቸው።  የፈተናው ውጤት ልጁን/ጅቷን በቋንቋ ድጋፍ መርሀግብር ውስጥ እንዲታቀፉ የሚያደርግ ከሆነ፣ ልጁ/ጅቷ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቃት ዓመታዊ ፈተና ላይ የማለፊያ ውጤት እስከሚያመጡ ድረስ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ በትምህርት ቤታቸው ውስጥ ልዩ ትምህርት ይሰጣቸዋል።  ከቋንቋ ድጋፍ መርሀግብር የሚወጡ ተማሪዎች ለአራት ዓመታት ያህል ለእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቁነት እና የትምህርት ይዘት ዕውቀት ላይ በፈተና ውጤታቸው መሰረት በትምህርት ቤታቸው ክትትል ይደረግባቸዋል።

ወላጆች እና አሳዳጊዎች ስለ የቋንቋ ድጋፍ መርሀግብር፣ የልጆቻቸው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ዕድገት፣ እና በልጆቻቸው ትምህርት ላይ እንዴት መሳተፍ እንደሚችሉ የበለጠ ለማወቅ የልጆቻቸው ትምህርት ቤት ቀርበው እንዲያነጋግሩ ይበረታታሉ።

የዲሲ የትምህርት ክፍያ እገዛ የገንዘብ ድጋፍ (DCTAG - ዲሲ.ቲ.ኤ.ጂ)

የዲሲ የትምህርት ክፍያ እገዛ የገንዘብ ድጋፍ (DCTAG - ዲሲ.ቲ.ኤ.ጂ) በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ላሉ ኮሌጅ ለመግባት ለሚፈልጉ ነዋሪዎች የከፍተኛ የትምህርት አማራጮችን ለማስፋፋት በ 1999 በኮንግረንስ የተፈጠረ ነው። ሁሉም የህዝብ ተቋማት፣ በታሪክ የጥቁር ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች (HBCUs)፣ እና በዋሽንግተን የከተማ ክልል ውስጥ ያሉ ለትርፍ ያልሆኑ የግል ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች በዲሲ.ቲ.ኤ.ጂ ውስጥ ለመሳተፍ ብቁ ናቸው።

ዲሲ.ቲ.ኤ.ጂ በአመሪካ፣ በጉዋም እና በፖርቶ ሪኮ በመላው ባሉ የህዝብ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በእስቴት ውስጥ እና ከእስቴት ውጭ መካከል መካከል ያሉ እስከ $10,000 የሚደርስ የትምህርት ክፍያ ልዩነቶችን በመደጎም ለዲስትሪክቱ ነዋሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ምርጫዎች ያሰፋል። በተጨማሪም ዲሲ.ቲ.ኤ.ጂ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በዲሲ የከተማ ክልል የሚገኙ የግል ኮሌጆች እና በመላው ሃገሪቱ ለሚገኙ የግል በታሪክ የጥቁር ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች (HBCUs) በዓመት እስከ $2,500 የአሜሪካ ዶላር የትምህርት ክፍያዎችን ይሰጣል። ዲሲ.ቲ.ኤ.ጂ በአሁኑ ወቅት ከ 300 በላይ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች አሉት። ኮሌጅዎ ወይም ዩኒቨርሲቲዎች ዲሲ.ቲ.ኤ.ጂ ውስጥ ይሳተፍ ወይም አይሳተፍ እንደሆነ ለማወቅ እባክዎትን በሚከተለው ድህረ ገጽ ላይ የተሳታፊ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝራችንን ይጎብኙ፥ https://osse.dc.gov/dctag

የሜየር የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት እድል ፕሮግራም

የሜየር የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት እድል ፕሮግራም በተመረጡ ቦታዎች ባሉ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በአስፈላጊነት ላይ የተመሰረተ የትምህርት ድጋፍ ብቁ ለሆኑ የተባባሪ ዲግሪ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ለሚከታተሉ የዲሲ ነዋሪዎች ይሰጣል። ፕሮግራሙ በተማሪው የገንዘብ ድጋፍ እና ትምህርቱን ለመከታተል በሚያስፈልጉት ወጪዎች መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት የተነደፈ ‘የመጨረሻ-ዶላር’ ሽልማት ነው። በተለምዶ፣ የሜየር ስኮላርሺፕ ተማሪዎች በአንድ የትምህርት ዘመን ላይ እስከ $4,000 የአሜሪካ ዶላር፣ ለተባባሪ ዲግሪ እስከ አራት ዓመት ድረስ፣ እና ለመጀመሪያ ዲግሪ ደግሞ እስከ ስድስት ዓመት ድረስ ያገኛሉ። የገንዘብ ድጋፉ ቀድሞ ለመጣ - ቀድሞ መስጠት በሚለው መርህ የሚሰጥ ሲሆን አመልካቾች በየዓመቱ ደግመው ማመልከት አለባቸው።

የሜየር የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት እድል ፕሮግራም በዲሲ የከተማ ክልል ውስጥ በተመረጡ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች ድጋፍ ይሰጣል። የትምህርት ድጋፉ ተቀባዮች ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ የሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማ ወይም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አቻ የምስክር ወረቀት (ለምሳሌ፥ GED) ያገኙ መሆን አለባቸው። ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት እባክዎትን የሜየር ስኮላርሺፕ ድህረ ገጽን ይጎብኙ፥ https://osse.dc.gov/mayorsscholars

ለኮሌጅ እና ለሥራ ዘርፍ ስምሪት የዝግጁነት ምዘና አጋርነት [The Partnership for Assessment of Readiness for College and Careers - PARCC]

ለኮሌጅ እና ለሥራ ዘርፍ ስምሪት የዝግጁነት ምዘና አጋርነት (The Partnership for Assessment of Readiness for College and Careers)፣ ወይም ፓርክ (PARCC)፣ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ዓመታዊ የሒሳብ እና ኢንግሊዘኛ (ELA) ፈተና ሲሆን፣ መሰረት ያደረገው መደበኛ ቁልፍ የግዛት መስፈርቶች [Common Core State Standards (CCSS)] ነው። የፓርክ (PARCC) ምዘናዎች ቁልፍ የትምህርት ቦታዎች ላይ የራስ መተማመን እና ስኬትን የሚያጎናጽፉት ሁሉንም ክህሎቶች—ውስብስብ ጽሁፎችን መረዳት፣ በማስረጃ የተደገፈ አፃፃፍ፣ የሒሳብ እንቆቅልሽ መፍታት — ለአብዛኛዎቹ ተማሪዎች የበለጠ አሳሳቢ የሆኑትን ዕውቀቶች እና ክህሎቶች ይመዝናል። ከ 3 እስከ 8 እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እያንዳንዱ ፀደይ ወቅት ላይ በድረገጽ በመጠቀም የእንግሊዘኛ (ELA) እና ሒሳብ የፓርክ PARCC ፈተናዎችን መውሰድ አለባቸው። የልጁን/ቷን ዕድገት ትልቁን ስዕል የሚያሳዩን — የውጤት ሪፖርት ካርድ፣ የክፍል ውጤት፣ እና የአስተማሪ ግብረመልስ ጨምሮ — አንድ ላይ በመሆን የፓርክ (PARCC) ውጤቶች ከብዙ መለኪያዎች ውስጥ አንዱ ነው። ለአስተማሪዎች እና ቤተሰቦች የተዘጋጁ ስለ ፓርክ (PARCC) ምዘና እና ግብዓቶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎን ከታች ያሉትን ግብዓቶች ይመልከቱ።

ከ 3 እስከ 8 እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እያንዳንዱ ፀደይ ወቅት ላይ በድረገጽ በመጠቀም የእንግሊዘኛ (ELA) እና ሒሳብ የፓርክ PARCC ፈተናዎችን። የልጁን/ቷን ዕድገት ትልቁን ስዕል የሚያሳዩን — የውጤት ሪፖርት ካርድ፣ የክፍል ውጤት፣ እና የአስተማሪ ግብረመልስ ጨምሮ — አንድ ላይ በመሆን የፓርክ (PARCC) ውጤቶች ከብዙ መለኪያዎች ውስጥ አንዱ ነው።

የተማሪዎች መጓጓዣ (OSSE DOT - ኦ.ኤስ.ኤስ.ኢ ዲ.ኦ.ቲ)

የተማሪ መጓጓዣ ክፍል (OSSE DOT- ኦ.ኤስ.ኤስ.ኢ ዲ.ኦ.ቲ) በዲስትሪክቱ ውስጥ የሚገኙ ብቁ የሆኑ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን በየቀኑ፣ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እና በሰዓቱ የሚያጓጉዝ ክልላዊ የትራንስፖርት ስርዓት ነው። ኦ.ኤስ.ኤስ.ኢ ዲ.ኦ.ቲ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ከሚገኙ አራት አውቶቡስ ማቆሚያዎች በመነሳት በየቀኑ በግምት እስከ 34,000 ማይሎች የሚጓዙ ከ 521 በላይ አውቶቡሶች አሉት።

የወላጅ የመረጃ ማዕከል (ስልክ ቁጥር፥ (202) 576-5000) የተማሪን የመጓጓዣ ጉዳይ በፍጥነት ተደራሽ በማድረግ ጥራት ያለው የደንበኛ አገልግሎት ለመስጠት በትጋት ይሰራል። የደንበኛ አገልግሎት ተወካዮች እስከ 20 ደቂቃዎች ወይም ከዛ በላይ የሚሆኑ የአውቶቡስ መዘግየቶችን በተመለከተ እና በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ወይም በሌሎች ድንገተኛ ሁኔታዎች ምክንያት የጉዞ መስመር እና መርሃግብር ለውጦችን ለተማሪዎች ወላጆች እና ለአሳዳጊዎች ለማሳወቅ ስልክ የሚደውሉ ይሆናል። ጥያቄዎች ለወላጅ የመረጃ ማዕከል በሚቀርቡበት ጊዜ የደንበኞች አገልግሎት ተወካዮች ተማሪው በዛ ቅጽበት ያለበትን ሁኔታ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት፣ ለወላጅ ስጋት መፍትሔ ለማግኘት እና ተገቢ የሆኑት የወላጆችን ጥያቄዎች ለመመለስ የጂፒኤስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም፣ ከጣቢያዎች እና ከሾፌሮች ጋር ይነጋገራሉ እንዲሁም በተማሪው መረጃ ላይ ጥናት ያደርጋሉ።

ለህጻን እንክብካቤ ለመክፈል እርዳታ፥ የህጻን እንክብካቤ ቫውቸር ፕሮግራም

የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ብቁ የሆኑ ቤተሰቦች ለልጆች እንክብካቤ አገልግሎቶች መክፈል እንዲችሉ የሚያግዝ በፌደራል መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት የልጆች እንክብካቤ እርዳታ ፕሮግራምን ያካሂዳል። የልጆች እንክብካቤ ቫውቸር ፕሮግራም ለቤተሰቦች የተለያዩ የሕጻናት እንክብካቤ አማራጮችን ይሰጣል። እነዚህ የተለያዩ መርሐ-ግብሮች እና ፕሮግራሞች መኖራቸው ቤተሰቦች ፍላጎታቸውን በተሻለ ሁኔታ የሚያሟላውን አማራጭ እንዲመርጡ ያስችላቸዋል።

ቤተሰቦችዎ የሰው ሃይል አገልግሎት መምሪያ፣ የኢኮኖሚ ደህንነት አስተዳደር የልጆች እንክብካቤ አገልግሎት ክፍል ጽ/ቤትን በስራ ሰዓት በመጎብኘት ለሕጻናት እንክብካቤ ቫውቸር ማመልከት ይችላሉ። በተጨማሪም እርስዎ በመረጡት ፍቃድ የተሰጠው ደረጃ II የልጆች እንክብካቤ አገልግሎት አቅራቢ በቀጥታ ማመልከት ይችላሉ (ተቋሙ ለመቀበል ፈቃድ ያለው መሆን አለበት)።

ድጋፍ የተደረገለት የሕፃናት እንክብካቤ አገልግሎት ማመልከቻ ካጠናቀቁ እና ካስገቡ በኋላ በመጀመሪያ የመቀበያ ጣቢያዎት ከብቁነት ሰራተኛ ጋር የቃለ መጠይቅ መርሃ ግብር ማዘጋጀት አለብዎት። በቃለ መጠይቁ ወቅት የብቁነት ሰራተኛው ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ ሁሉንም ተገቢ የብቁነት መመዘኛዎች በደንብ ይገነዘባል። ፕሮግራሙ ብቁ ለሆኑ ህፃናት ከ 6 ሳምንት እስከ 12 ዓመታት ድረስ አገልግሎት ይሰጣል። ነገር ግን የአካል ጉዳት ያለባቸው ልጆች እስከ 19ኛ ዓመት ልደታቸው ድረስ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

የልጆች እንክብካቤ ድጎማ ለሚቀበሉ ልጆች እንክብካቤ መስጠት ይፈልጋሉ?

  1. የልጅ እንክብካቤ ድጎማ አቅራቢ ስለመሆን መረጃ ለማግኘት የቅድመ ትምህርት መምሪያን ያነጋግሩ። ለዚህ ፕሮግራም ለማመልከት የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የልጆች እድገት አገልግሎት ሰጪ ሆነው ፍቃድ ያለዎት መሆን አለብዎት። ፈቃድ ያለው የልጆች እንክብካቤ አቅራቢ ስለመሆን መረጃ ያግኙ።
  2. በልጆች እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም ውስጥ እንዲሳተፉ የተፈቀደላቸው አቅራቢዎች ከተፈቀደላቸው አገልግሎት የመስጠት አቅማቸው እስከ 95 በመቶ ድረስ የድጋፍ ቫውቸር የሚቀበሉ ቤተሰቦችን እንዲያገለግሉ ይፈቀድላቸዋል። ስምምነቱ በቅድመ ልጅነት ትምህርት መምሪያ በጽሁፍ ፍቃድ እስኪያገኝ ድረስ ለተሰጠ የልጆች እንክብካቤ አገልግሎት ክፍያ ተመላሽ ሊደረግልዎት አይችልም።

ጠንካራ ጅማሬ ዲሲ ቅድመ ጣልቃ ገብነት መርሀግብር [Strong Start DC Early Intervention Program (DC EIP)]

ጠንካራ ጅማሬ የዲሲ ቅድመ ጣልቃ ገብነት መርሀግብር የአካለ ስንኩልነት እና የዕድገት መዘግየት ያለባቸው ለጨቅላ ሕፃናት እና ለዳዴ ለሚሉ ልጆች እና ለቤተሰቦቻቸው ቅድመ ጣልቃ ገብነት ቴራፒ አገልግሎት የሚሰጥ አገር አቀፍ፣ ሁሉን አቀፍ፣ ዘርፈ ብዙ ሙያዎች የሚሳተፉበት ነው። የፌደራል የአካለ ስንኩልነት ያለባቸው ግለሰቦት የትምህርት አዋጅ [federal Individuals with Disabilities Education Act (IDEA)] ክፍል ሐ፣ ከዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሕዝብ ሕግ 1-2-119 ጋር በመሆን ልዩነት ለማምጣት በበቂ ሁኔታ አስቀድሞ አካለ ስንኩልነት ያለባቸው ጨቅላ እና ዳዴ የሚሉ ሕፃናት እና ቤተሰቦቻቸው የተቀናጀ  አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ስልጣን አለው። እነዚህ አገልግሎቶች ተለዋዋጭ፣ ከባህል ጋር የሚሄዱ፣ እና በጣም አስፈላጊ በሆነ ሁኔታ፣ የልጆቹን እና የቤተሰብ ፍላጎቶችን ማሟላት አለባቸው።

የጠንካር ጅማሬ ቅድመ ጣልቃገብነት መርሀግብር በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሚኖሩ ጨቅላ እና ዳዴ የሚሉ ሕፃናት ቤተሰቦቻቸው ዕድገታቸው ላይ ስጋት ያለባቸው ከሆነ እንደ ብቸኛ የመግቢያ መንገድ ያገለግላል። ስለ ጨቅላ ወይም ዳዲ የሚሉ ሕፃናት ስጋቶች ያለዎት እንደሆነ፣ ስትሮንግ ስታርት ቻይልድ ፋይንድ (Strong Start Child Find ) የስልክ መስመርን በ (202) 727-3665 ስልክ ቁጥር ላይ ይደውሉ።

ማይ ስኩል ዲሲ (My School DC)፥ በዲሲ ውስጥ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች አማራጮችን ይፈልጉ

ማይ ስኩል ዲሲ (My School DC) ለሁሉም ዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (DCPS) ትምህርት ቤቶች እና ከክፍል PK3 እስከ through 12 ድረስ ተሳታፊ ለሆኑ የሕዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች መደበኛ መተግበሪያ ነው። DCPS ትምህርት ቤቶች (በእነሱ ክልል ውስጥ ያሉ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ) የክፍል PK3 ወይም PK4 መርሀግብር ለሚፈልጉ ተማሪዎች፥ ከክልል ውጪ ያሉ ወይም በመላው ከተማ ውስጥ ለሚገኙ የ DCPS ትምህርት ቤቶች (PK3-12)፥ የ DCPS የተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ወይም መርሀግብር (9-12)፥ ወይም የሕዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች (PK3-12) የማይ ስኩል ዲሲ (My School DC) መተግበሪያ ያስፈልጋል። ይጎብኙ የ ማይ ስኩል ዲሲ ድረገጽ ስለ ከተማው የሕዝብ ትምህርት ቤቶች አማራጮች ለማወቅ እና ለማመልከት። ጋፍ ለማግኘት የማይ ስኩል ዲሲን የስልክ መስመር (My School DC hotline) (202) 888-6336 ስልክ ቁጥር ላይ በሳምንቱ ሥራ ቀናት ከጠዋቱ 8- ከሰዓቱ 5 ድረስ በመደወል ያግኙ ወይም በዚህ አድራሻ [email protected] ኢሜይል በመፃፍ ጥያቄ ያቅርቡ።

በትምህርት ቤት ለመመዝገብ የዲሲ ነዋሪ መሆንዎትን ያረጋግጡ

በማንኛውም የዲሲ የሕዝብ ትምህርት ቤት ውስጥ ለመመዝገብ፣ ወላጅ ወይም የመጀመሪያ እንክብካቤ ሰጭ በዲስትሪክቱ ውስጥ በባህላዊ የህዝብ ወይም ህዝባዊ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ለተመደበ ወይም መማር ለሚፈልግ ለእያንዳንዱ ተማሪ የዲሲ ነዋሪነትን ማረጋገጫ ዋና ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው። ነዋሪነትን ለመወሰን በትክክል የተጠናቀቀ የዲሲ የነዋሪነት ማረጋገጫ ቅጽ መሞላት አለበት።

ከሚከተሉት አንዱ የዲሲ ነዋሪነትን ለመመስረት ተቀባይነት አለው፥

  • የደሞዝ ክፍያ ማስረጃ፣
  • ተጨማሪ የደህንነት ገቢ ዓመታዊ የጥቅማጥቅ ማሳወቂያ፣
  • በዲሲ የግብር እና የገቢ ጽ/ቤት የተረጋገጠ የ D40 ቅጽ ቅጂ፣
  • የወታደር የመኖሪያ ቤት ትእዛዝ፣
  • የኤምባሲ ደብዳቤ፣
  • ልጁ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ክልል ውስጥ እንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃ፣ በፍርድ ቤት ትእዛዝ መልክ፣ እና
  • ከዲሲ መንግሥት የገንዘብ እርዳታ መኖሩን ማረጋገጫ፣ ከሚከተሉት በአንዱ መልክ፥
  • ለችግረኛ ቤተሰቦች ጊዜያዊ እርዳታ (TANF - ቲ.ኤ.ኤን.ኤፍ) የገቢ ማረጋገጫ ማሳወቂያ ወይም በድጋሚ ብቁ ለመሆን የማረጋገጫ/የማጽደቂያ ደብዳቤ፣
  • የሜዲክኤይድ የማጽደቂያ ደብዳቤ ወይም በድጋሚ ብቁ ለመሆን የማጽደቂያ ደብዳቤ፣
  • የተጠሪውን ስም እና ስልክ ቁጥር የያዘ ከመጠለያ ቤቶች የተሰጠ የመኖሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ፣ ወይም ከመኖሪያ ቤቶች ባለስልጣን የተሰጠ ደብዳቤ፣ ወይም
  • ከሌላ የዲሲ መንግሥት ፕሮግራም የሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ መኖሩን ማረጋገጫ።

የዲሲ ነዋሪነትን ለማረጋገጥ ከላይ የተገለጹት አንዳቸውም ሰነዶች መቅረብ ካልቻሉ፣ ከሚከተሉት ሁለቱ ያስፈልጋሉ፥

  • ጊዜው ያላለፈበት የዲሲ የሞተር ተሽከርካሪ ምዝገባ፣
  • ጊዜው ያላለፈበት የሊዝ ውል ወይም የኪራይ ስምምነት፣
  • ጊዜው ያላለፈበት የዲሲ የሞተር ተሽከርካሪ የስራ ፈቃድ ወይም ሌላ የመንጃ ፍቃድ ያልሆነ ህጋዊ መታወቂያ፣ እና
  • የቤት ውስጥ የፍጆታ ክፍያ ደረሰኝ (የጋዝ፣ የመብራት እና የውሃ ደረሰኞች ብቻ ተቀባይነት ያላቸው)።

ነዋሪነትን ለመወሰን ኦ.ኤስ.ኤስ.ኢ ተጨማሪ ሰነዶችን ሊጠይቅ ይችላል። የነዋሪነት ሁኔታን ለማረጋገጥ ቤተሰቦች ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ሰነዶች እንዲያቀርቡ ሊጠየቁ ይችላሉ፥

የዲሲ ነጻ የበጋ ምግብ ፕሮግራም

የዲሲ ነጻ የበጋ የምግብ ፕሮግራም ትምህርት ቤት በሚዘጋበት ወቅት በሰኔ፣ በሐምሌ እና ነሐሴ ወራት ለልጆች ነጻ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና ቀለል ያሉ ምግቦችን (ስናክ) ለመመገብ የተነደፈ የፌዴራል የምግብ ፕሮግራም ነው። የምግብ አገልግሎት ለማግኘት ምንም ማመልከቻ የማያስፈልግ ሲሆን ፕሮግራሙ እድሜያቸው 18 ዓመት እና ከዚያ በታች ለሆኑ ልጆች ሁሉ ነጻ ነው። አገልግሎቱን ለማግኘት ልጆች በምግብ ሰዓት የዲሲ ነጻ የበጋ ምግብ ጣቢያን መጎብኘት ብቻ ይጠበቅባቸዋል። ዲሲ ነጻ የበጋ ምግብ ጣቢያዎች የዩ.ኤስ.ዲ.ኤ (USDA) መመሪያዎችን የሚያሟሉ የተመጣነ ይዘት ያላቸውን ምግቦች ያቀርባሉ። ብዙ የመመገቢያ ጣቢያዎች በተጨማሪም ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አዝናኝ እና ጠቃሚ እንቅስቃሴዎችን ያቀርባሉ። ለእርስዎ ቅርብ የሆነ የዲሲ ነጻ የበጋ ምግብ ጣቢያን ከዚህ ድህረ-ገጽ ያግኙ፥ https://www.fns.usda.gov/summerfoodrocks

የግጭት መፍትሄ ሰጭ ጽ/ቤት፥ የፍትህ ሂደት ችሎት ጥያቄ

የአካል ጉዳት ያለባቸው ግለሰቦች ትምህርት ሕግ (IDEA - አይ.ዲ.ኢ.ኤ) የአካል ጉዳተኞች ልጆች ወላጆች እና የሕዝብ የትምህርት ኤጄንሲዎች የአካል ጉዳት ያለባቸውን ልጆች ለይቶ በማወቅ፣ በመገምገም፣ የትምህርት ምደባ በመስጠት ወይም ነጻ የሆነ ተስማሚ የሕዝብ ትምህርት ለልጁ በማቅረብ ዙሪያ የተፈጠሩ አለመስማማቶችን ለመፍታት የሚያስችል አድሏዊ ያልሆነ የይግባኝ ፍትህ የችሎት ጥያቄ ለማንሳት እድሉ ያላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአሰራር ሂደት እያንዳንዱ እስቴት እና የኮሎምቢያ ዲስትሪክት እንዲመሰርቱ እና እንዲጠቀሙ ይጠይቃል። በእስቴት የትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ጽ/ቤት (OSSE- ኦ.ኤስ.ኤስ.ኢ) ስር የሚገኘው የግጭት መፍትሄ ሰጭ ጽ/ቤት የልዩ ትምህርት የፍትህ ችሎት ሂደት የማካሄድ ኃላፊነት አለበት።

የልዩ ትምህርት የይግባኝ ችሎት ሂደት ለወላጆች እና ለሕዝብ የትምህርት ኤጀንሲው አለመግባባቱ ባስከተለው ጉዳይ (ጉዳዮቹ) ዙሪያ ያላቸውን አመለካከት እና ሃሳብ ስልጠና ለወሰደ፣ ገለልተኛ ለሆነ እና ለማያዳላ የሰሚ ችሎት መኮንን በምስክሮች እና ሰነዶች በተጨባጭ ለማሳየት እድሉን ይሰጣቸዋል። የይግባኝ ችሎቱ ባለስልጣናት የዲስትሪክቱ የህዝብ ትምህርት ሥርዓት ቅጥር ሰራተኞች አይደሉም። ችሎቱ ከተካሄደ በኋላ፣ የይግባኝ ሰሚ ባለስልጣኑ አለመግባባት ባስከተሉት ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፤ ይህንንም ለወላጅ እና ለሕዝብ የትምህርት ኤጀንሲው ያሳውቃል። የፍትህ ሂደት ችሎት ውሳኔ በፍርድ ቤት ይግባኝ ሊባል ይችላል።

አይ.ዲ.ኢ.ኤ የፍትህ ሂደት ችሎት በሚጠይቁበት ጊዜ ሁለቱም ወገኖች የተወሰኑ አካሂዶችንን እንዲከተሉ የሚያስገድድ ሲሆን ወላጅ፣ የሕዝብ የትምህርት ኤጀንሲው፣ እና የችሎት አቤቱታ ሰሚ መኮንኑ ሊከተሏቸው የሚገቡ የተወሰኑ የጊዜ ገደቦች እና ደንቦች አሉ። ይህ አሰራር በሚከተላቸው የአሰራር ሂደቶች እና የፍርድ ሂደቱ ሕጋዊ ባህሪ መኖር ምክንያት፣ አብዛኛውን ጊዜ ወላጆች የሚወክላቸው ጠበቃ ይኖራቸዋል፣ ነገር ግን ራሳቸውን መወከልም ይችላሉ።

ለቤተሰቦች እና ለተማሪዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ የግጭት መፍትሄ ሰጭ ጽ/ቤት ድህረ ገጽን ይጎብኙ፥ osse.dc.gov/service/office-dispute-resolution-odr

የጎዳና ተዳዳሪ ትምህርት መርሀግብር

የጎዳና ተዳዳሪዎች የትምህርት መርሀግብር ተልዕኮ ለጎዳና ተዳዳሪ ልጆች እና ወጣቶች ነፃ፣ ተገቢ፣ የሕዝብ የትምህርት ዕድል መፍጠር፥ ለትምህርት ቤቶች ፣ መጠለያዎች እና ለማህበረሰቡ የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት፥ እና የጎዳና ተዳዳሪዎችን ችግሮች እንዲሰሙ ማድረግ ናቸው። የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች እና ወጣቶች እንደ የጎዳና ተዳዳሪ ያልሆኑ ልጆች እና ወጣቶች እኩል የሆነ የትምህርት ዕድል ማግኘት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም፣ ጎዳና ተዳዳሪ ልጆች እና ወጣቶች ሁሉም ተማሪዎች የሚገጥማቸውን ተመሳሳይ ፈታኝ የትምህርት ስኬት መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።

የቋንቋ ተደራሽነት አገልግሎቶች፥

ለንግግር ቋንቋ አስተርጓሚ እና/ወይም ለትርጉም፣ እባክዎትን የኤጀንሲውን የቋንቋ ተደራሽነት አስተባባሪን ያነጋግሩ፥

ኤልሳ ተክለሃይማኖት - በኢሜይል፥ [email protected] ወይም በስልክ፥ (202) 727-6436

አድራሻ፥

Office of the State Superintendent of Education
1050 First St. NE
Washington, DC 20002
ስልክ፥ (202) 727-6436