Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

osse

Office of the State Superintendent of Education
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የዲሲ የልጅ እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም

የልጆች እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም የዲሲ ቤተሰቦች ለልጅ እንክብካቤ ወጪ እንዲከፍሉ ይረዳል። ፕሮግራሙ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች በዲስትሪክቱ ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት እና እንክብካቤ እንዲያገኙ ይደግፋል።

ለቤተሰቦች መረጃ
የልጅ እንክብካቤ ቫውቸር ለመቀበል፣ አንድ ቤተሰብ ማመልከቻ መሙላት እና ማስገባት አለበት። ማመልከቻው እንደ አስፈላጊነት ደረጃ፣ ገቢ እና የቤተሰብ መጠን ባሉ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት የቤተሰብን ብቁነት ለመወሰን ይጠቅማል። የልጆች እንክብካቤ ድጎማ የሚያገኙ ቤተሰቦች ልዩ የጥራት ደረጃዎችን የሚያሟሉ ፈቃድ ካላቸው ሰፊ የልጆች እንክብካቤ አቅራቢዎች መካከል መምረጥ ይችላሉ። በልጆች እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም ውስጥ ከ250 በላይ የልጆች እንክብካቤ አቅራቢዎች ስለሚሳተፉ፣ የዲሲ ቤተሰቦች ፍላጎታቸውን የሚያሟላ የልጅ እንክብካቤን ማግኘት እና መጠቀም ይችላሉ።

እንዴት ነው ማመልከት የምቻለው
ቤተሰቦች ለዲሲ የልጅ እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም በመስመር ላይ፣ በአካል በዲሲ የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ (DHS) ወይም በአካል በደረጃ II የልጅ የእንክብካቤ ሰጪ ተቋም ማመልከት ይችላሉ ። በተጨማሪም፣ ቤት እጦት ያጋጠማቸው ቤተሰቦች በቨርጂንያ ዊሊያምስ የቤተሰብ መርጃዎች ማእከል ማመልከት ይችላሉ። እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ላይ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል

ጥያቄ ላላቸው ወይም ማመልከቻውን ለመሙላት እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች ድጋፍ አለ። ቤተሰቦች ለድጋፍ ወደ DHS ወይም የደረጃ II የልጅ እንክብካቤ አቅራቢን በአካል መጎብኘት ወይም DC Child Care Connections በ (202) 829-2500 ወይም [email protected] ማግኘት ይችላሉ።

መርጃዎች ለቤተሰቦች

መረጃ ለልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች
በልጅ እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ እና የልጅ እንክብካቤ ቫውቸሮችን የሚያገኙ ቤተሰቦችን ለማገልገል፣ የልጅ እንክብካቤ አቅራቢ በስቴት ትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ቢሮ (OSSE) ጽሕፈት ቤት ፈቃድ ማግኘት እና በOSSE የተመደበውን የድጎማ ስምምነት ሂደት ማጠናቀቅ አለበት። በድጎማ ፕሮግራሙ ላይ እንዲሳተፉ የተፈቀደላቸው አቅራቢዎች የህፃናት ማቆያ ቫውቸሮችን የሚቀበሉ ቤተሰቦችን በተፈቀላቸው አቅም 100 በመቶ ማገልገል ይችላሉ።

በድጎማ ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ፈቃድ ያላቸው የልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል አለባቸው።

  1. የድጎማ አቅጣጫ-አሰጣጥ ፕሮግራሙን ያጠናቅቁ። እዚህ የሚገኙትን እርምጃዎች ይከተሉ።
  2. የድጎማ አቅራቢ ማመልከቻውን ይሙሉ። የድጎማ አቅጣጫ-አሰጣጥ መርሃ ግብሩን ያጠናቀቁ የልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች እንዲሞሉ እና ከደጋፊ ሰነዶች ጋር እንዲያስገቡ ማመልከቻ ይላክላቸዋል።
  3. የድጎማ ስምምነቱን ይሙሉ። ማመልከቻቸው የጸደቀላቸው የልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች ለፊርማ የድጎማ ስምምነት ይላክላቸዋል።

መርጃ ለልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች

Contact Phone: 
(202) 727-3557
Contact Fax: 
(202) 741-5403
Contact TTY: 
711
Contact Suite #: 
Sixth Floor
Office Hours: 
Monday to Friday, 8:30 a.m. to 5:30 p.m.
Service Location: 

1050 First Street, NE

GIS Address: 
1050 First Street, NE
City: 
Washington
State: 
DC
Zip: 
20002