Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

osse

Office of the State Superintendent of Education
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የቅድመ-ልጅነት የሰው-ኋይል የትምህርት መስፈርቶች፦ ዳራ እና የኋላ ታሪክ

የመጀመሪያዎቹ ሶስት የህይወት አመታት ለልጅ አእምሮ በጣም ፈጣን እና ወሳኝ የእድገት ጊዜ ናቸው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የቅድመ ልጅነት ተሞክሮዎች ልጆች ለትምህርት ቤት እንዲዘጋጁ እና የዕድሜ ልክ፣ አወንታዊ ተፅእኖዎች እንደሚኖራቸው እና የአስተማሪ ብቃት በ በጥራት ላይ ተፅእኖ መኖሩን ነው።

 

የኦፊስ ኦፍ ዚ ስቴት ሱፐርኢንተንደንት ኦፍ ኤጁኬሽን ቢሮ የመጀመሪያ ተማሪዎች ንቁ እና ጥራት ያላቸው የቅድመ ትምህርት ከባቢዎች እንዲያገኙ እና ለ K-12 ትምህርታቸው ዝግጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነው። በዲሴምበር 2016፣ OSSE በዲስትሪክቱ ውስጥ ላለ የቅድመ ልጅነት የስራ ሃይል የትምህርት መስፈርቶችን የሚጨምሩ የዘመኑ የልጅ እንክብካቤ ፈቃድ መስጫ ደንቦችን አሳትሟል። የትምህርት መስፈርቶቹ በOSSE ፍቃድ በተሰጣቸው የልጅ እድገት ተቋማት ውስጥ ለ ማዕከል ዳይሬክተሮችአስተማሪዎችረዳት አስተማሪዎችየቤት ተንከባካቢዎች እና ተባባሪ የቤት ተንከባካቢዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ። እነዚህ የትምህርት መስፈርቶች ለምን እና እንዴት እንደወጡ ተጨማሪ መረጃ ከዚህ የበታች ይገኛል።

 

ለእያንዳንዱ የሰራተኛ አይነት በተወሰኑ መስፈርቶች ላይ፣ እንዲህም የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች ለስራ ደረጃቸው የትምህርት መስፈርቶችን እንዲያሟሉ የቀረቡ መርጃዎችን እና ድጋፎችን በተመለከተ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ

ዳራ እና የኋላ ታሪክ

OSSE በእንክብካቤ ውስጥ ያሉ ህጻናትን ጤና፣ ደህንነት እና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም የልጆችን ትምህርት የሚያሳድጉ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የመማሪያ አካባቢዎችን እና ተሞክሮዎችን ለማዳበር አላማ ለቅድመ ልጅነት የስራ ሃይል ዝቅተኛውን የትምህርት መስፈርቶች ጨምሯል። በመተዳደሪያ ደንቡ ውስጥ የተካተቱት የትምህርት መስፈርቶች ሁሉም የቅድመ-ልጅነት አስተማሪዎች በልጆች እድገት ላይ ስልጠና እንዲኖራቸው እና በዋና መምህር ፣ የተስፋፋ የቤት ውስጥ ተንከባካቢ እና የዳይሬክተር ሚናዎች ላይ ያሉት ለህፃናት ከፍተኛ ጥራት ያለው የትምህርት ልምዶችን ለመፍጠር አስፈላጊ የሆኑ ተጨማሪ እውቀት እና ክህሎቶች እንዲኖራቸው በማረጋገጥ፣ እና ሌሎች ሰራተኞች ጥራት ያለው የቅድመ ትምህርት ፕሮግራሞችን እንዲሰጡ በመቆጣጠር እነዚህን ግቦች ይደግፋሉ።

የ2016 የፈቃድ መስጫ ደንቦች ዝማኔዎች የተዘጋጁት የዲስትሪክቱን የተለያዩ የቅድመ ትምህርት ዘርፍ ከሚወክሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከር የተዘጋጁ እንዲሁም በልጆቻችንን መንከባከብ ላይ በተቀመጡት የተመራማሪዎች፣ የሃኪሞች እና የባለሙያዎች እውቀት ከተዘጋጁ ምክረ ሃሳቦች ጋር የተጣጣሙ ነበሩ፦ ብሔራዊ የጤና እና የደህንነት አፈጻጸም ደረጃዎች፥ የቅድመ እንክብካቤ እና ትምህርት ፕሮግራሞች መመሪያዎች

ደንቦቹ በ2016 ከታተሙበት ጊዜ ጀምሮ፣ OSSE የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች ለሰራተኞቻቸው አይነት የሚጠይቀውን የትምህርት መስፈርት እንዲያሟሉ ብዙ ጊዜ ቀነ ገደቦችን አራዝሟል። ይህ በመጀመሪያ የተደረገው የስራ ሃይሉ ማስረጃዎችን እንዲያገኝ ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት ሲሆን በተጨማሪ የተራዘመው የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሺኙን ተጽዕኖዎች በመረዳት ነው። በዲሴምበር 2፣ 2022፣ ለማዕከል ዳይሬክተሮች የትምህርት መስፈርቱ ተግባራዊ ሆነ። ለሁሉም የሰራተኛ አይነቶች የትምህርት መስፈርቶች ከዲሴምበር 2፣2023 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናሉ።

OSSE ለበርካታ አመታት የትምህርት መስፈርቶችን እንዲያሟሉ ለቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች መርጃዎችን እና ድጋፎችን ሰጥቷል። ይህ የቅድመ ልጅነት አስተማሪ (ECE) እገዛ ዴስክ መፍጠርን እና የልጅ እድገት ተባባሪ (CDA) የስልጠና እና የዝግጅት ፕሮግራም እንዲሁም የ DC መሪ አስተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ዲግሪ (DC LEAD) ፕሮግራም የመሳሰሉ ፕሮግራሞች መጀመርን ያጠቃልላል። የቅድመ ልጅነት የሰው ሃይል መርጃዎች እና ድጋፎችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ማግኘት ይቻላል።

የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች ለሰራተኞቻቸው አይነት የትምህርት መስፈርቱን እንዲያሟሉ መርጃዎችን እና ድጋፎችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።

ተያያዥ ይዘቶች፥