የ DC የመሪ አስተማሪዎች ለከፍተኛ ዲግሪ (DC LEAD) እርዳታ አላማ ለዲስትሪክቱ ልጆች እንክብካቤ አስተማሪዎችን ከ DC ታዳጊ ተማሪዎች ጋር ለመስራት ከሚያስፈልገው እውቀት፣ ክህሎቶች እና ማስረጃዎች ጋር ለማቅረብ እና ለሁለተኛ ደረጃ ዲግሪዎች በነጻ የትምህት እድል በኩል በዲስትሪክቱ ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የቅድመ ልጅነት ባለሙያዎችን ቁጥር ለመጨመር ነው። የሳውዝ ኢስት የልጆች ፈንድ (SCF) በስቴት የትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ቢሮ (OSSE) ቅድመ ትምህርት ክፍል (DEL) በኩል የDC LEAD ስጦታ ተቀባዩ ነው እና የእርዳታ ፕሮግራሙን ያስተዳድራል።
በ SCF በኩል፣ የ DC LEAD ፕሮግራም በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ላሉ የልጅ እንክብካቤ አስተማሪዎች በተባባሪ እና/ወይም በመጀመሪያ ዲግሪ በቅድመ ልጅነት ትምህርት (ECE) የኮርስ ስራ እንዲያጠናቅቁ ነጻ የትምህርት እና ማበረታቻ ይሰጣል ለ፦
- ለወጣት ልጆች እና ለቤተሰቦች ከፍተኛ-ጥራት ያለው ቅድመ እንክብካቤን እና ትምህርትን በማረጋገጥ የልጅ እድገት ፕሮግራም አገልግሎቶችን ለማሻሻል፤
- በ ECE ክፍሎች ውስጥ ልምዶችን ለማሻሻል ማስረጃዎችን ለማግኘት እና አቅምን ለመጨመር፤
- የአሁኑን አነስተኛ የትምህርት መስፈርቶች ለማሟላት፤
- የሰራተኞች አያያዝን ለማሻሻል፤ እና
- ካሳ ለመጨመር።
የ DC LEAD ነጻ የትምህርት እድል እና የማበረታቻ ፕሮግራም የተጀመረው በረቡዕ፣ ጁን 8፣ 2022 ነው። የልጅ እንክብካቤ አስተማሪዎች፣ በOSSE እና SCF ድህረ ገጾች የDC LEAD ድህረ ገጽን በመጎብኘት የDC LEAD ነጻ የትምህርት እድል እና የማበረታቻ ማመልከቻን ማግኘት ይችላሉ። የOSSE እና የSCF ድህረ ገጾች በተጨማሪም ስለ DC LEAD ነጻ የትምህርት እድል እና ማበረታቻ ፕሮግራም የብቁነት መስፈርቶች እና ማመልከት የሚችሉበትን መንገድ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣሉ።
ከ DC LEAD ወይም ከልጆች እንክብካቤ አስተማሪዎች ጋር ለተያያዙ ጥያቄዎች፣ እባክዎ በ[email protected] ወይም በ(202) 561-5500 የDC LEAD ቡድን ያነጋግሩ። እንዲሁም በ[email protected] ወይም በ(202) 478-5903 የ OSSE ECE የእርዳታ ዴስክን ማነጋገር ይችላሉ።
ተያያዥ ይዘቶች፥