Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

osse

Office of the State Superintendent of Education
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የDC የትምህርት ክፍያ ድጋፍ ስጦታ (DCTAG)

ደረጃ 1

ለDCTAG መዘጋጀት ማለት የብቁነት መስፈርቶችን መገምገም፣ ለማመልከቻው የሚፈልጉትን መረጃ መሰብሰብ፣ እና ጥቂት ተጨማሪ ደረጃዎችን መሙላት ማለት ነው። እርስዎ እና/ወይም ቤተሰብዎ ግብርዎን መሙላት፣ FAFSAዎን ማስገባት እና ምናልባትም ከሌሎች የዲሲ ኤጀንሲዎች ሰነዶችን ማግኘት ይኖርብዎታል።

ማንኛውንም ስኮላርሺፕ ወይም ችሮታ ሲያስቡ ጥሩ የመጀመሪያ እርምጃ ብቁ መሆንዎን ማየት ነው። DCTAG ለእያንዳንዱ አመልካች ለማሟላት የሚያስፈልጉ ባህሪያት ዝርዝር፣ እና የትኞቹ ትምህርት ቤቶች የDCTAG ሽልማቶችን መቀበል እንደሚችሉ መረጃ አለው። ይህ ገጽ በተጨማሪም ቴክኒካዊ ቃላትን ለማብራራት ወይም የሰነድ ምሳሌን ለእርስዎ ለማሳየት ማስፈንጠሪያዎች አሉት።

 1. ለኮሌጅ DCTAG ማግኘት እችላለሁ (እኔ ብቁ ነኝ)?
 2. ለመከታተል ባሰብኩበት ኮሌጅ የDCTAG ሽልማቴን መጠቀም እችላለሁ?
 3. ምን ዓይነት ሰነዶች ናቸው የሚያስፈልጉኝ?

a. የግብር ሰነዶቼን ከየት ማግኘት እችላለሁ?
b. የሰነዶችን ምሳሌ ልታሳዩኝ ትችላላችሁ?

 1. ለማወቅ የሚገቡ ቃላት

a. ዶሚስል - የት ነው የሚኖሩት?
b. የሚጠበቅ የቤተሰብ መዋጮ (EFC)
c. የተማሪ ድጋፍ ሪፖርት (SAR)
d. የፍርድ ቤት ዋርድ

1. ለኮሌጅ DCTAG ማግኘት እችላለሁ (እኔ ብቁ ነኝ)?

የDCTAG አመልካቾች የሚከተሉት መሆን አለባቸው፥

 • የ US ዜጋ ወይም ብቁ ዜጋ-ያለመሆን ሁኔታ መኖር፤
 • ብቁ የህዝብ ወይም የግል ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲን የሚከታተል፤
 • የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ኗሪ አመልካቹ መጀመሪያ ኮሌጅ ከመግባቱ በፊት ቢያንስ ለ12 ተከታታይ ወራት፣ እና በአመልካቹ የኮሌጅ ማትሪክ ውስጥ ቀጣይ መኖሪያን መያዝ (ማስታወሻ፥ የጥገኛ ተማሪዎች [እድሜያቸው ከ24 በታች የሆነ] መኖሪያ በወላጅ ወይም አሳዳጊ ይቋቋማል)፤
 • በፌዴራል የተማሪ ብድር ያልተከፈለ ሁኔታ ውስጥ አለመሆን፤
 • የሁለተኛ ደረጃ ምሩቅ ወይም አጠቃላይ ተመጣጣኝ ዲፕሎማ (GED) ተቀባይ፤
 • እንደ መደበኛ ዲግሪ ፈላጊ ተማሪ፣ ቢያንስ፣ ለግማሽ ጊዜ መሰረት፣ ለመመዝገብ ተቀባይነት ያለው ወይም ለመጀመሪያው የአንደኛ ዲግሪ ላይ እየሰራ ያለ፤
 • ባችለር ዲግሪ ያላገኘ ወይም ያልተቀበለ ሰው፤
 • ፕሮፌሽናል ወይም የድህረ-ምረቃ ደረጃ ዲግሪ እጩ ያልሆነ፤
 • በአጥጋቢ አካዳሚክ ማሻሻል (SAP) መሰረት በኮሌጅ/ዩኒቨርስቲ የምዝገባ ወይም ተቀባይነት ያለው ምዝገባ እንደተተረጎመ፤
 • 26 ዓመት እድሜ ወይም ከዚያ በታች፤ እና
 • በ DCTAG ከፍተኛ የገቢ ጣሪያዎች መሰረት። የገቢ ደረጃን በሽልማት ዓመት እና በድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመጀመሪያ አመት ለማወቅ፣ እባክዎ ይህንን መመሪያ ይከልሱ - የDCTAG ከፍተኛ ገቢ [እባክዎ ይህ ሰነድ የተሻሻለው ኖቨምበር 18፣ 2022 እንደሆነ ይገንዘቡ። ጥያቄዎች ካለዎት፣ እባክዎን የእርስዎን DCTAG አማካሪ ያነጋግሩ።]

በተጨማሪም፣ በኮሌጃቸው ወይም በዩኒቨርሲቲያቸው የስቴት ክፍያ የሚከፍሉ ተማሪዎች DCTAG ለመቀበል ብቁ አይደሉም። የDCTAG ተቀባዮች ሽልማቶችን በመቀበል ቢበዛ ለስድስት ዓመታት የተገደቡ ናቸው እና በዓመት ከሚፈቀደው ከፍተኛ የሽልማት መጠን ወይም የህይወት ዘመን ከፍተኛ የሽልማት መጠን በላይ ላያገኙ ይችላሉ (እነዚህ እንደ ተቋም ዓይነት ይለያያሉ - እባክዎን የተማሪዎች እና ቤተሰቦች ሽልማቶችን ይመልከቱ) ለዝርዝሮች )።

2. ለመከታተል ባሰብኩበት ኮሌጅ የDCTAG ሽልማቴን መጠቀም እችላለሁ?

ይህ የDCTAG ተሳትፎ ስምምነት ባለፈው ጊዜ የፈረሙ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች (ተቋማት) ዝርዝር ነው። የሚማሩበትን ወይም ለመከታተል የሚፈልጉትን ተቋም ካላዩ፣ እና ብቁ በሆነ ምድብ ውስጥ የሚገኝ ከሆነ (ከዚህ በታች ይመልከቱ)፣ እባክዎትን የስቴት ትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ (OSSE) ድህረ ሁለተኛ ደረጃ እና የሙያ ትምህርት (PCE) በ (202) 727-2824 ያነጋግሩ። PCE ተቋሙን ያነጋግራል።

የDCTAG ብቁ የሆኑ ተቋማት፥ በUS ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የህዝብ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች፤ በUS ውስጥ ያሉ የህዝብ እና የግል ታሪካዊ ጥቁር ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች (HBCU's)፤ በዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮፖሊታን አካባቢ የሚገኙ ሁሉም የግል፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች። ለንግድ ስራ የተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ብቁ አይደሉም።

ለንግድ ስራ የተቋቋሙ ተቋማት በውስጥ ገቢ አገልግሎት የሚገለጹት ለትርፍ የተቋቋሙ ተቋማት ናቸው ተብለው ነው።

3. ምን ዓይነት ሰነዶች ናቸው የሚያስፈልጉኝ?

ቀደም ብሎ መጀመር ከDCTAG የጊዜ ገደብ በፊት የገቡ ሁሉንም ሰነዶችን ለማግኘት የስኬት ቁልፍ ነው! በማረጋገጫ ዝርዝሩ ላይ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ማስገባት የDCTAG ሰራተኞች የግምገማ ሂደቱን እንዲጀምሩ ያስችላቸዋል።

ለDCTAG ብቁ መሆንዎን ለማረጋገጥ የDCTAG ቡድን ያስገቡትን ሰነዶች ማረጋገጥ አለበት።

የDCTAG አመልካቾች የአስፈላጊ ሰነዶችን PDF ወይም JPGs ወደ DC OneApp መጫን ይችላሉ። ሁሉም ሰነዶች በተመሳሳይ ጊዜ መጫን አለባቸው። ለዚህም ነው ሁሉንም ሰነዶች አስቀድመው ማዘጋጀትዎ አስፈላጊ የሆነው። ሰነዶችን ስለማስገባት ተጨማሪ መረጃ በአመልክት እና አስገባ ገጽ ላይ ይገኛል።

ጠቃሚ ፍንጮች፥ በዚህ ጊዜ፣ ሁሉም ማመልከቻዎች በኤሌክትሮኒክ መንገድ መቅረብ አለባቸው። የDCTAG አማካሪዎች በኢሜል ይከታተላሉ።

የማረጋገጫ ዝርዝሩ (በቅርቡ በብዙ ቋንቋዎች ይገኛል) እና የምሳሌ ሰነዶቹ ይህ ሂደት ለእርስዎ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲሄድ እንደሚረዱት ተስፋ እናደርጋለን።

3a. የግብር ሰነዶቼን ከየት ማግኘት እችላለሁ?

በኦንላይን የDCTAG ማመልከቻን የሚሞሉ ብዙ ተማሪዎች ትክክለኛውን የD-40 ግብር መልስ እንደ መኖሪያ ቤት እና ገቢ መስፈርቶች ማሟያ ማስረጃ ከማመልከቻው ጋር ማያያዝ ይችላሉ። ይህ ሂደት ለብዙ ቤተሰቦች የግብር መረጃን ለDCTAG ሲያጋሩ የሚጠቀሙበት የቅድሚያ አማራጭ መሆን አለበት። እንዳስፈላጊነቱ ዕርዳታ እና ድጋፍ ለማግኘት እባክዎ የእርስዎን የተማሪ DCTAG አማካሪ ያግኙ።

በተጨማሪም፣ DCTAG ለግብር ሰነዶች አማራጮችን አክሏል - እባክዎን የዚህን የሽልማት ዓመት ልዩ ሁኔታዎች የማረጋገጫ ዝርዝሩ ላይ ይከልሱ።

DC OneApp ግብሮችዎን ሰርስሮ ማውጣት ካልቻለ እና የተረጋገጠ ወይም የተረከበ እና የተሟላ የD-40 ግብር መልስን ማግኘት ካልቻሉ፣ ሌሎች የመኖሪያ ቤት ማረጋገጫ ቅጾችን፣ የሚያስፈልጉ የድጋፍ ሰነዶች የማረጋገጫ ዝርዝር ውስጥ የተዘረዘሩትን፣ ማስገባት እንደሚችሉ እባክዎ ያስታውሱ።

ስለዚህ ወይም ሌሎች ሂደቶች ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉዎት የDCTAG አማካሪዎን ያነጋግሩ።

3b. የሰነዶቹን ምሳሌ ልታሳዩኝ ትችላላችሁ?

አዎ። አመልካቾች የDCTAG ማመልከቻቸውን ለመሙላት እነዚህ ሁሉ ሰነዶች ግዴታ አያስፈልጋቸውም፣ ነገር ግን በማረጋገጫ ዝርዝሩ ውስጥ እርስዎ ሊያውቁት የማይችሉት ሰነድ ካለ፣ ይህ እሽግ የምንጠይቀው እያንዳንዱ ሰነድ ምሳሌ አለው። ዓመቱ በተጨባጭ ትክክል ላይሆን ይችላል - እነዚህ የእይታ ምሳሌዎች ብቻ ናቸው።

የሰነዶች ምሳሌ

4. ለማወቅ የሚገቡ ቃላት

4a. መኖሪያ ቦታ - የት ነው የሚኖሩት?

ለDCTAG ብቁ ለመሆን፣ አመልካቹ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ቢያንስ ለ12 ወራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የአንደኛ ዓመት ትምህርት መከታተል ከመጀመሩ በፊት መኖሪያ ቤት መመስረት አለበት። ለሙሉ ብቁነት መስፈርቶች እባክዎን የዲሲ ኮድ፣ ርዕስ 38፣ ምዕራፍ 27 እና የዲሲ ማዘጋጃ ቤት ደንቦች፣ ርዕስ 29፣ ምዕራፍ 70 ይመልከቱ። በኮሎምቢያ ዲስትሪክት፣ መኖሪያ ቦታ የሚለው ቃል በዲስትሪክት የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ለመመዝገብ ብቁነትን ለማረጋገጥ ጥቅም ላይ ሲውል “ኗሪነት” ከሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው።

ዶሚሳይል (መኖሪያ ቦታ) ማለት የአንድ ሰው ቋሚ የመኖሪያ ቦታ ነው። ስለሆነም፣ መኖሪያ ቤት የሁለት ነገሮች ጥምረት ነው፥ (1) ትክክለኛ መኖሪያ እና (2) የመቆየት ፍላጎት።

የፌደራል ህግ የDCTAG ሽልማቶችን የሚያገኙ አመልካቾች በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ እንዲኖሩ ያስገድዳል። ግለሰቦች የመኖሪያ ቦታን ሳያሳዩ በዲስትሪክቱ ውስጥ የፖስታ ሳጥን ሊያገኙ ስለሚችሉ፣ OSSE የፖስታ ሳጥን ቁጥርን ተቀባይነት ያለው አድራሻ አድርጎ አይመለከተውም።

እባክዎ ያስታውሱ፥ በዲሲ የሕዝብ ትምህርት ቤት ውስጥ መመዝገብ የተለየ መስፈርት አለው እና ለDCTAG ብቁነት ዓላማ መኖሪያ ቤት አያቋቁምም። ለብቻ የሆነ የምዝገባ መስፈርቶችን እዚህ መገምገም ይችላሉ።

4b. የሚጠበቅ የቤተሰብ መዋጮ (EFC)

EFC ማለት ለመቀበል ብቁ የሚሆኑበት የፌደራል የተማሪ ዕርዳታ መጠን ለማስላት በኮሌጅዎ ወይም በዩኒቨርስቲዎ ጥቅም ልይ የሚውል ቁጥር ነው። EFC የሚሰላው የቤተሰብዎ ግብር የሚጣልበት እና የማይጣልበት ገቢ፣ ንብረት፣ እና ጥቅማጥቅሞችን (እንደ ስራ አጥነት ወይም ማህበራዊ ዋስትና ያሉ) የሚጠቀም ቀመር በመጠቀም ነው። ቀመሩ በተጨማሪም የቤተሰብዎን ብዛት እና በዓመቱ ኮሌጅ የሚማሩትን የቤተሰብ አባላት ብዛት ግምት ውስጥ ያስገባል።

በእርስዎ FAFSA ላይ የሚያጋሩት መረጃ የእርስዎን EFC ለማስላት ጥቅም ላይ ይውላል። ትምህርት ቤቶች የእርስዎን የፌዴራል የተማሪ እርዳታ ብቁነት እና የገንዘብ ድጋፍ ሽልማት ለመወሰን EFC ይጠቀማሉ።

የእርስዎ EFC የግድ ቤተሰብዎ ለኮሌጅ የሚከፍሉት የገንዘብ መጠን አይደለም፣ እና እርስዎ የሚቀበሉት የፌዴራል ተማሪዎች እርዳታ መጠንም አይደለም።

4c. የተማሪ ድጋፍ ሪፖርት (SAR)

የእርስዎ የተማሪ ድጋፍ ሪፖርት (SAR) ለፌደራል የተማሪ እርዳታ ብቁ መሆንዎን እና እንዲሁም ለ FAFSA ጥያቄዎች የእርስዎን መልሶች የሚዘረዝር አንዳንድ መሰረታዊ መረጃዎችን የሚሰጥ ወረቀት ወይም ኤሌክትሮኒክ ሰነድ ነው። የእርስዎን SAR በመስመር ላይ ወይም በወረቀት ላይ የሚቀበሉት በእርስዎ FAFSA ቅጽ ላይ የኢሜይል አድራሻ ባቀረቡ ላይ ነው የሚወሰነው።

የFSA መታወቂያ (የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል) ካለዎት እና የ FAFSA መረጃዎ ከተሰራ፣ በመስመር ላይ ወይም በወረቀት FAFSA ቅፅ ላይ ማስገባትዎ ወይም የኢሜል አድራሻ ማቅረብዎ ወይም አለማቅረብዎ ከግምት ውስጥ ሳይገባ የSAR መረጃዎን ለማየት በ fafsa.gov መግባት ይችላሉ።

ከላይ ባሉት ሰነዶች ውስጥ የምሳሌ  SAR አለ።

4d. የፍርድ ቤት ዋርድ

የፍርድ ቤቱ ዋርድ ወይም የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ዋርድ ማለት እንክብካቤ እንዲሰጠው እና ኃላፊነት እንዲወስድለት በፍርድ ቤት የተሾመ ሞግዚት የተመደበለት ሰው (ብዙውን ጊዜ ለአካለ መጠን ያልደረሰ) ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ሞግዚቱ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ሊሆን ይችላል። እኛ – “በዲሲ በዋርድ (1-8) ትኖራለህ?” ማለታችን አይደለም።


ማስታወሻ፥ [PDF] ይህ ሰነድ በተንቀሳቃሽ ሰነድ ቅርጸት (PDF) ይቀርባል። የ PDF አንባቢ ለእይታ አስፈላጊ ነው።

ተያያዥ ይዘቶች፥

የDCTAG ተማሪዎች እና ቤተሰቦች
DCTAG ያመልክቱ እና ያስገቡ
የDCTAG ሽልማቶችን ያዘጋጃል