የቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያ በቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች እና በእነሱ የK-12 አቻዎች መካከል ወጥ የሆነ ክፍያ ማግኘትን ለማሳካት ያለመ የመጀመሪያው ሃገር አቀፍ ፕሮግራም ነው። የቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያ እንዴት እንደተዘጋጀ እና እንዴት እየተተገበረ እንዳለ ከዚህ በታች የበለጠ ይወቁ።
ቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያ፦ የጊዜ ሰሌዳ እና የኋላ ታሪክ
- ኦገስት 2021፦ የበጀት አመት 2022 (FY22) የ2021 የበጀት ድጋፍ የድንገተኛ ጊዜ ማሻሻያ ህግ የቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያን በግዛት የትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ቢሮ (OSSE) እንዲተዳደር እና የልጅ እድገት ተቋም ሰራተኞችን ካሳ ለመጨመር ጥቅም ላይ እንዲውል እንደ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት መንግስት ልዩ የገንዘብ ድጋፍ አዘጋጅቷል። እንዲሁም ህጉ የገንዘብ ድጋፉን ተግባራዊ ለማድረግ ምክረ ሃሳቦችን እንዲያቀርብ የቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የካሳ ቡድን (ቡድን) ፈጠረ።
- ኦክቶበር 2021-አፕሪል 2022፦ የቡድኑ አባላት የቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያን ተግባራዊ ለማድረግ ምክረሃሳቦችን ለማዘጋጀት ተገናኝተው ባለድርሻ አካላትን አሳትፈዋል።
- ጃንዋሪ 2022፦ ቡድኑ የቡድኑን ምክረ ሃሳቦች ከግምት የሚያስገቡ የሰአት ክፍያዎችን ብቁ ለሆኑ የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች ለመክፈል ከOSSE ጋር ስምምነት ላደረጉ የልጅ እድገት ተቋማት የገንዘብ ድጋፎችን የሚያሰራጭ የረጅም ጊዜ ስርዐት በሚዘረጋበት ጊዜ፣ በFY22 ብቁ ለሆኑ የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች የአንድ ጊዜ ክፍያ ማሟያዎችን ለማሰራጨት OSSE ከወኪል ድርጅት ጋር አብሮ እንዲሰራ የሚመክር ሪፖርት አሳትሟል።
- ፌብሩዋሪ 2022፦ የቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የካሳ ቡድን ጊዜያዊ ማሻሻያ ህግ ቡድኑ ባቀረባቸው ምክረ ሃሳቦች መሰረት ወጥ የሆነ ክፍያን ለመደገፍ ለቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፎችን እንዲከፍል ለOSSE ስልጣን ሰጥቷል።
- ማርች፣ 2022፦ ቡድኑ ባላቸው የስራ መደቦች እና የትምህርት ማስረጃዎች መሰረት ለቅድመ አስተማሪዎች የሚኖር ዝቅተኛ የካሳ ደረጃዎችን በተመለከተ ተጨማሪ ምክረሃሳቦችን የሚያቀርብ የመጨረሻ ሪፖርት አሳትሟል።
- ጁላይ 2022፦ የቡድኑ ምክረሃሳቦች በዲሲ ምክር ቤት በበጀት አመት 2023 የ 2022 የበጀት ድጋፍ ህግ፣ የዲሲ ህግ 24-470 ውስጥ የተካተተ ሲሆን ይህም OSSE በFY23 ብቁ ለሆኑ የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች ቀጥተኛ ክፍያዎችን ማከፋፈሉን እንዲቀጥል ስልጣን ሰጥቷል።
- ኦገስት 2022-ሴፕቴምበር 2023፦ ተጨማሪ ክፍያዎች ብቁ ለሆኑ የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች ተከፋፍለዋል።
- ዲሴምበር 2023፦ OSSE ብቁ ለሆኑ የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች እንደ መደበኛ ክፍያቸው አካል ክፍያን ለመጨመር ተሳታፊ ለሆኑ የልጅ እድገት ተቋማት በየሩብ አመቱ ገንዘብ ማከፋፈል ጀምሯል።
- ፌብሩዋሪ 2024፦ OSSE የቅድሚያ ልጅነት አስተማሪ ክፍያ እኩልነት ፈንድ ቀጣይ ትግበራን ለማሳወቅግብረ ኃይሉን በድጋሚ ጠራ።
- ጁን 2024፦ የዲሲ ካውንስል የበጀት ድጋፍ ህግን (BSA) አጽድቋል ይህም ግብረ ኃይሉ ለከንቲባ እና ለዲሲ ካውንስል ሪፖርት እንዲያቀርብ በፕሮግራሙ ላይ የሚደርሱትን የፊስካል ጫናዎች በ28 በጀት አመት እንዲገደቡ ምክረ ሃሳቦችን የያዘ ሲሆን ይህም ዝቅተኛውን የደመወዝ ለውጥ እና የገንዘብ ድጋፍ ቀመርን ጨምሮ ለ25 በጀት አመት እና የወደፊት የበጀት ዓመታት።
- ሴፕቴምበር 2024፦ ግብረ ኃይሉ ለFY25 ዝቅተኛውን ደሞዝ እና የህፃናት ማጎልበት ተቋም (ሲዲኤፍ) የደመወዝ ክፍያ ቀመርን ለማሻሻል ምክሮችን የያዘ ሪፖርት አውጥቷል።
- ኦክቶበር 2024፦ የዲሲ መማክርት ጉባኤ የቅደመ ልጅነት አስተማሪ ክፍያ ሚዛን ድንገተኛ ማስተካከያ አዋጅ 2024ን ያጸደቀ ሲሆን ይህም አዋጅ ዝቅተኛውን የቅደመ ልጅነት ማስተማር ተቋማት ብቁ ለሆኑ እና በግብረሀይሉ ጥቆማ መሰረት ለሰራተኞቻቸው መክፈል ያለባቸውን መጠን የሚወስን ነው።
FY22 እና FY23፦ ተጨማሪ ክፍያዎች
OSSE ለFY22 እና FY23 የቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያን ለማስተዳደር፣ በደረጃው ቀልጣፋ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራሞችን ለማስተዳደር ከተዘጋጀ ማህበራዊ ተጽዕኖ ከሚያደርግ ኩባንያ፣ AidKit ጋር እየሰራ ነው። AidKit ማመልከቻውን አቅርቧል፣ የገንዘብ ድጋፎችን ሰጥቷል እንዲሁም ለአመልካቾች የቴክኒክ ድጋፍ አድርጓል።
በFY22፣ ብቁ የሆኑ የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች በሰራተኛ አይነታቸው (ለምሳሌ፣ መምህር፣ ረዳት መምህር፣ የቤት ውስጥ ተንከባካቢ፣ ወዘተ) እና በቅጥር ሁኔታቸው (ለምሳሌ፣ የሙሉ ጊዜ ወይም የትርፍ ጊዜ) ላይ በመመስረት ለአንድ ክፍያ እስከ $14,000 ድረስ ተቀብለዋል። በFY23፣ ብቁ የሆኑ የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች በሰራተኛ አይነታቸው እና በቅጥር ሁኔታቸው ላይ በመመስረት በኦክቶበር 2022 እና በሴፕቴምበር 2023 መካከል እያንዳንዳቸው $3,500 የሚደርሱ እስከ አራት ክፍያዎች ተቀብለዋል።
በአጠቃላይ፣ OSSE እና AidKit በFY22 እና FY23 ከ4000 በላይ ለሚሆኑ አስተማሪዎች ከ$80 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ገንዘብ አከፋፈለዋል። በFY22 እና FY23 የቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያን በሚመለከት የበለጠ ለማወቅ እዚህ ጠቅ ያድርጉ።
FY24 እና ከዚያ በላይ፦ የልጅ እንክብካቤ ቀጣሪዎች ክፍያ እንዲጨምሩ መደገፍ
ከFY24 ጀምሮ፣ OSSE ለቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች በ AidKit ቀጥተኛ ክፍያዎችን መክፈል አቁሞ በልጅ እድገት ተቋም (CDF) የደመወዝ ክፍያ የገንዘብ ድጋፍ ቀመር አማካኝነት የገንዘብ ድጋፎችን ለልጅ እድገት ተቋማት ማከፋፈል ጀምሯል። ከCDF የደመወዝ ክፍያ የገንዘብ ድጋፍ ቀመር ገንዘቦችን ለመቀበል፣ የልጅ እድገት ተቋማት በOSSE ፍቃድ የተሰጣቸው እና ብቁ ለሆኑ የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች፣ በሥራ መደብ እና በከፍተኛ የትምህርት ማስረጃ፣ በOSSE የተቋቋመውን ዝቅተኛ ደመወዞች የሚያሟሉ ወይም የሚበልጡ ደሞዞችን ለመክፈል መስማማት አለባቸው። የልጅ እድገት ተቋማት በቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያ ውስጥ እንዲሳተፉ አይገደዱም። ስለ ቅድመ ልጅነት አስተማሪ ፍትሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያ ወቅታዊ አተገባበር የበለጠ ለማወቅ እዚህ ጠቅ ያድርጉ።