Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

osse

Office of the State Superintendent of Education
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የልጅ እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ለቤተሰቦች፥ ስለ ብቁነት እና እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ የበለጠ ይወቁ!

አዲስ! የዲሲ ቤተሰቦች በመስመር ላይ ለልጅ እንክብካቤ ድጎማዎች ማመልከት ይችላሉ። ማመልከቻውን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

የልጅ እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም ምንድን ነው?

 የልጅ እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም፣ እንዲሁም የልጅ እንክብካቤ ቫውቸር ተብሎ የሚታወቀው፣ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢዎች ያላቸው የዲሲ ቤተሰቦች ለልጅ እንክብካቤ ወጪ እንዲከፍሉ እና በ ዲስትሪክት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያለው የቅድመ ትምህርት እና እንክብካቤ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። ልጅዎ ለልጅ እንክብካቤ ድጎማ ብቁ ከሆነ፣  የድጎማ ፕሮግራሙ የልጅ እንክብካቤ ወጪዎችዎን በሙሉ ወይም በከፊል ለህፃናት እንክብካቤ አቅራቢው ይከፍላል። በቤተሰብዎ ገቢ ላይ በመመስረት፣ የወጪውን የተወሰነ ክፍል እንዲከፍሉ ሊጠየቁ ይችላሉ።

 

የልጅ እንክብካቤ ቫውቸር የት መጠቀም እችላለሁ?

ቤተሰቦች ቫውቸሮችን በሚቀበል ፈቃድ ባለው የልጅ ልማት ተቋም ውስጥ ለእንክብካቤ ለመክፈል የልጆች እንክብካቤ ድጎማዎችን መጠቀም ይችላሉ። ቤተሰቦች MyChildCare.dc.govን በመጠቀም ወይም DC Child Care Connectionsን በ (202) 829-2500 ወይም በ[email protected] ቫውቸሮችን የሚቀበሉ የልጅ እድገት ተቋማት ዝርዝርን ማግኘት ይችላሉ።

በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ቤተሰቦች በተጨማሪም ፈቃድ ባላቸው የቤት-ውስጥ እንክብካቤ አቅራቢዎች ለሚሰጠው የልጅ እንክብካቤ ክፍያ ለመክፈል ቫውቸሮችን ሊጠቀሙ ይችላሉ። የቤት-ውስጥ እንክብካቤ አቅራቢ በልጁ ቤት ውስጥ ልጅን ለማንከባከብ በወላጅ ወይም በአሳዳጊ የሚመረጥ አቅራቢ ነው። የቤት-ውስጥ እንክብካቤ አቅራቢን ለመጠቀም፣ ወላጅ/አሳዳጊ የመርሃግብር ፍላጎታቸውን ወይም የልጃቸውን ፍላጎቶች የሚያሟላ ፈቃድ ያለው የልጅ እድገት ማእከል ወይም የልጆች ማሳደጊያ ቤት ጋ እንክብካቤ ማግኘት እንዳልቻሉ ማሳየት አለባቸው።

በቤት-ውስጥ እንክብካቤ አቅራቢዎች ቤተሰቡ ድጎማ የሚደረግበት የልጅ እንክብካቤ አገልግሎት ለማግኘት ብቁ እንደሆነ ከተወሰነለት በኋላ በልጆች እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም ውስጥ ለመሳተፍ ከስቴት ትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ቢሮ (OSSE) ጋር ስምምነት ማድረግ አለባቸው።

 

የልጅ እንክብካቤ ቫውቸር ለመቀበል ብቁ የሚሆነው ማነው?

ለልጅ እንክብካቤ ድጎማ ብቁ መሆን በአስፈላጊነት ደረጃ፣ በገቢ እና በቤተሰብ ብዛት ግምገማ ላይ የተመሰረተ ነው። አብዛኛዎቹ ቤተሰቦች የገቢ ብቁነት መስፈርቶችን በማሟላት እና የልጁ ወላጅ(ጆች) ወይም ተቀዳሚ ተንከባካቢ(ዎች) በስራ ላይ ወይም በትምህርት ቤት ሲሆኑ የልጅ እንክብካቤ እንደሚያስፈልግ በማሳየት ለልጅ እንክብካቤ ድጎማ ብቁ ይሆናሉ። ለገቢ ብቁ ከሆኑ ቤተሰቦች በተጨማሪ osse.dc.gov/publication/child-care-subsidy-program-parent-fee-final-rules፣ የልጅ እንክብካቤ እርዳታ  እንዲሁም ለሚከተሉት ይገኛል፥

  • ጊዜያዊ እርዳታ ለተቸገሩ ቤተሰቦች (TANF) ጥቅማጥቅሞችን የሚያገኙ እና በግለሰብ ሀላፊነት እቅዶች መሰረት በትምህርት እና ስልጠና ላይ የሚሳተፉ ቤተሰቦች፤
  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ ዲግሪ የሚፈልጉ ታዳጊ ወላጆች፤ እና/ወይም
  • TANF የማያገኙ ነገር ግን የስራ እድሎችን እና ተስፋዎችን ለማሻሻል ተጨማሪ ትምህርት የሚከታተሉ ቤተሰቦች፤
  • የምግብ ስታምፕ የሥራ ቅጥር ስልጠና ፕሮግራም ተሳታፊዎች፤
  • በማደጎ ወይም በመከላከያ አገልግሎቶች ውስጥ ያሉ ልጆች፤
  • ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች፤
  • የአካል ጉዳተኛ አዋቂ ልጆች፤
  • የሙያ ማገገሚያ አገልግሎት ተቀባይ ወላጅ ልጆች፤
  • የመኖሪያ ቤት ማጣት ያጋጠማቸው ልጆች፤
  • የTANF ተከፋይ።

ለድጎማ ጥቅማጥቅሞች የሚፈቀደው ከፍተኛ ገቢ ምን ያህል ነው?

እስከ 300 በመቶ የፌደራል የድህነት ደረጃ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች፣ ወይም በ2023 አራት አባላት ላሉት ቤተሰብ 90,000 ዶላር፣ የልጆች እንክብካቤ ድጎማዎችን ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። አንድ ቤተሰብ ለድጎማ ብቁ ከሆነ በኃላ፣ ገቢያቸው ቢጨምርም እንኳን—እስከ 85 በመቶው የዲሲ ሚዲያን ገቢ፣ ወይም በ2023 ለአራት አባላት ቤተሰብ $129,000፣ ድጎማውን ማቆየት ይችላሉ።

በኦክቶበር 1፣ 2023፣ OSSE ለዲሲ ቤተሰቦች ለድጎማ ብቁ ለመሆን የገቢ ብቁነት መቁረጫን ከ250 የፌዴራል የድህነት ደረጃ ወደ 300 በመቶ ጨምሯል፣ ይህም ለልጅ እንክብካቤ ድጎማ ብቁ የሚሆኑ የልጆች እና ቤተሰቦች ቁጥርን ሰፋ ያደርጋል። አዲሱ የተንሸራታች ክፍያ መለኪያ እዚህ ይገኛል።

አንድ ቤተሰብ ለድጎማ ብቁ የሚሆንበት ትክክለኛ የገቢ ደረጃ በቤተሰብ አባላት ብዛት፣ በእንክብካቤ ላይ ያሉ ልጆች ቁጥር እና የገቢ መጠን ይወሰናል። ከገቢ በተጨማሪም፣ ቤተሰቦች ቫውቸር ለመቀበል  ሌሎች መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው። የእርስዎን ልዩ የብቁነት ምድብ ለመወሰን እባክዎ DHSን ወይም ስልጣን ያለው ደረጃ II የልጅ እንክብካቤ አቅራቢን ያነጋግሩ።

የልጅ እንክብካቤ ቫውቸር ለመቀበል የት እና እንዴት ማመልከት እችላለሁ?

ለዲሲ የልጅ እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም ለማመልከት አራት መንገዶች አሉ።

  1. በመስመር ላይ፥ ማመልከቻ ለማስገባት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። ማመልከቻዎን ካስገቡ በኋላ፣ እንደ ደረሰ የሚያሳውቅ እና እርስዎን ከብቁነት ሰራተኛ ጋር የሚያገናኝ የኢሜይል ማሳወቂያ ከሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ (DHS) ይደርስዎታል። የማመልከቻውን ሂደት ለማጠናቀቅ ከብቁነት ሰራተኛዎ ጋር ለቃለ-መጠይቅ ቀጠሮ መያዝ አለብዎት። በስልክ ቃለ-መጠይቁ ወቅት፣ የብቁነት ሰራተኛው ለቤተሰብዎ ሁሉም ተገቢ የሆኑ የብቁነት ሁኔታዎችን የበለጠ ለመረዳት ጥያቄዎችን ይጠይቃል።
  2. በአካል በሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ (DHS)፥ በ 4049 South Capital St. SW, Washington, DC 20032 የሚገኘውን DHS፣ የኢኮኖሚ ደህንነት አስተዳደር፣ የልጅ እንክብካቤ አገልግሎቶች ክፍልን ይጎብኙ። አመልካቾች ቀጠሮ ለመያዝ ወደ DHS በ (202) 727-0284 እንዲደውሉ ይበረታታሉ። የተወሰኑ በአካል-የመምጣት ጉብኝቶች ለአዲስ አመልካቾች በመጀመሪያ የመጣ፣ በመጀመሪያ ይገለገላል መሰረት፣ ሰኞ፣ ማክሰኞ እና እሮብ፣ ከ8፡15 ኤ.ኤም-3፡30 ፒ.ኤም ይገኛሉ። ከጉብኝትዎ በፊት እዚህ የሚገኘውን የልጅ እንክብካቤ ድጎማ ማመልከቻን እንዲያትሙ እና እንዲሞሉ ይበረታታሉ። ነጻ የህትመት አገልግሎቶች በቤተ-መፃህፍት ካርድ በዲሲ የህዝብ ቤተ-መፃህፍት ይኖራሉ።
  3. በአካል በደረጃ II የልጅ እንክብካቤ አቅራቢ ተቋም፥ የልጅ እንክብካቤ ድጎማ ቅበላ ሂደትን ለማጠናቀቅ የተፈቀደለትን ተቋም ይጎብኙ። የደረጃ ሁለት ተቋማት ዝርዝር እዚህ ይገኛል። ከጉብኝትዎ በፊት እዚህ የሚገኘውን የልጅ እንክብካቤ ድጎማ ማመልከቻን እንዲያትሙ እና እንዲሞሉ ይበረታታሉ። ነጻ የህትመት አገልግሎቶች በቤተ-መፃህፍት ካርድ በዲሲ የህዝብ ቤተ-መፃህፍት ይኖራሉ።
  4. በአካል በቨርጂኒያ ዊሊያምስ የቤተሰብ መርጃ ማዕከል፥ የመኖሪያ ቤት እጦት ያጋጠማቸው ቤተሰቦች በ920-A Rhode Island Ave. NE, Washington, DC 20018 የሚገኘውን የመርጃ ማእከል ሰኞ እና እሮብ ከ8፡15 ኤ.ኤም እስከ 4፡45 ፒ.ኤም መጎብኘት ይችላሉ።

በምሽት እና/ወይም ቅዳሜና እሁድ የምሰራ ከሆነ፣ ድጎማ ለሚደረግ የልጅ እንክብካቤ ማመልከት እችላለሁን?

አዎ፣ በልጅ እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም ውስጥ የሚሳተፉ አንዳንድ የልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች በምሽት፣ ማታ እና ቅዳሜና እሁድ አገልግሎት ይሰጣሉ። ቤተሰብዎ ባህላዊ ያልሆነ የልጅ እንክብካቤ አገልግሎት ከፈለገ፣ በDHS ማመልከት እና የተግባር መርሃ ግብርዎን የማመልከቻዎ አካል አድርገው ማቅረብ አለብዎት።

ማመልከቻውን ለመሙላት የት ጥያቄዎችን መጠየቅ ወይም ድጋፍ ማግኘት እችላለሁ?

ጥያቄ ላላቸው ወይም ማመልከቻውን ለመሙላት እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች ድጋፍ አለ። ቤተሰቦች ለድጋፍ ወደ DHS ወይም የደረጃ ሁለት የልጅ እንክብካቤ አቅራቢን በአካል መጎብኘት ወይም DC Child Care Connections በ (202) 829-2500 ወይም [email protected]ማነጋግር ይችላሉ።

ድጎማ ለሚደረግለት የልጅ እንክብካቤ ማመልከቻ አካል አድርጌ ማቅረብ የሚኖርብኝ ምን ዓይነት ሰነዶች ናቸው?

ከእያንዳንዱ የማረጋገጫ ምድብ ቢያንስ አንድ ሰነድ ማቅረብ አለብዎት።

የማረጋገጫ ምድብ

የማረጋገጫ ሰነዶች

የአመልካች ማንነት

  • የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የመንጃ ፍቃድ
  • ተቀባይነት ያለው የመንግስት መታወቂያ ካርድ
  • የUS ፓስፖርት

የዜግነት እና የህግ ሁኔታ ማረጋገጥ

  • ህጋዊ ቋሚ የመኖሪያ ካርድ
  • የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈ I-94 ወይም ሌላ የስደተኛ ምዝገባ ካርድ
  • የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈ ቪዛ

ሊቆጠር የሚችል ቤት ማረጋገጫ

  • ሁለት በተከታታይ ቀን የተጻፈባቸው የክፍያ መግለጫዎች፤ የመጨረሻው መግለጫ በመግቢያዎ 30 ቀናት ውስጥ መፃፍ አለበት እና ስምዎን ፣ የተከፈለበትን ቀን እና ገቢዎን ከመቀነሱ በፊት ያሳዩ
  • አዲስ የተቀጠሩ ከሆነ ወይም የክፍያ መግለጫዎችዎ ከኢንተርኔት ከወረዱ ወይም ሁሉንም አስፈላጊ መረጃዎች ካልያዙ በ30 ቀናት ውስጥ ከአሰሪዎ የተሰጠ መግለጫ
  • በግል ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለገቢ እና ለግብር ዓላማዎች የተያዙ ተመሳሳይ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው፣ ከእነዚህም መካከል የሚከተሉትን ጨምሮ፥
    • ሥራ ላይ ያለው የዲሲ ንግድ ፍቃድ
    • የሕዝብ-ተሽከርካሪ-ለኪራይ ኦፕሬተር ዕለታዊ ምዝግብ ማስታወሻ (ገለጻ) ቢያንስ ለአራት ሳምንታት
  • የፀጉር አስተካካይ እና የኮስሞቶሎጂ ፈቃድ ፣ የዳስ ኪራይ እና የመሳሪያ ኪራይ መዛግብት ወይም የቀጠሮ መርሃ ግብሮች እና የቀን የሽያጭ መዝገቦች ከቅርብ ቀናት ጋር።
  • የመንገድ ላይ ሻጭ ፍቃድ፣ የአቅርቦት ግዢ እና የእለት ሽያጭ መዝገብ እና የኪራይ እቃዎች ደረሰኞች ከቅርብ ቀናት ጋር

ሌላ ሊቆጠር የሚችል ገቢ ማረጋገጫ

  • እንደ ማህበራዊ ዋስትና እና የቀድሞ ወታደሮች ጥቅማጥቅሞች ያሉ ሌሎች የወላጅ(ዎች) ወይም የአሳዳጊ(ዎች) ገቢዎች
  • የሥራ አጥነት ወይም የሰራተኞች ማካካሻ
  • እንደ የልጅ ማሳደጊያ ወይም የማህበራዊ ዋስትና ገቢ ያሉ ድጎማ የሚደረግበት እንክብካቤ የሚያገኙ ልጆች ገቢ
  • የፍቺ የቀለብ ክፍያዎች

የህጻን እንክብካቤ ፍላጎት

  • በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ለልጁ ወላጅ(ዎች) ወይም አሳዳጊ(ዎች) ስራ፣ ስልጠና እና/ወይም የትምህርት ቤት መርሃ ግብር። የልጅ ወይም የአመልካች የአካል ጉዳተኝነት ማረጋገጫ። መርሃ ግብሮች ከተለያዩ፣ ሰነዱ ይህንን የሚያንፀባርቅ መሆን አለበት።

በአመልካች እና ጥቅማጥቅሞችን እያገኘ ያለው ልጅ መካከል ያለውን ግንኙነት ማረጋገጥ

  • ልጅን ለተፈጥሮ ወላጅ፣ በፍርድ ቤት ለተሾመ አሳዳጊ ለማረጋገጥ የሚያስፈልግ ሰነድ፣ ከTANF የተከፈለ ክፍያ ሰነድ፣ ወይም ከእርምት መምሪያ ወይም ልጅን በጊዜያዊነት የማሳደግ መብትን የሚሰጥ ሌላ የወንጀለኛ መቅጫ ሥርዓት ሰነድ
  • የልደት የምስክር ወረቀት - ለአገልግሎቶች የሚያመለክቱ ወላጅ ስምን ያካትታል
  • የሆስፒታል የልደት መዝገብ - ከ 6 ወር በታች ለሆኑ ህጻናት፣ ኦፊሴላዊ የምስክር ወረቀት በ 30 ቀናት ውስጥ መቅረብ አለበት
  • ከተፈቀደ የዲሲ የመንግስት ኤጀንሲ ወይም ከአቅራቢው የተላከ ሪፈራል

የመኖሪያ ማረጋገጫ

  • ኦፊሴላዊ የኪራይ ደረሰኝ - በኩባንያው ቅጽ ወይም በደብዳቤ ራስ ላይ
  • የቤት ባለቤትነት ማስረጃ - የአሁኑ የሞርጌጅ ክፍያ
  • የኪራይ ውል ወይም የመኖሪያ ቤት ድጎማ ሰነድ
  • የፍጆታ ክፍያ - PEPCO፣ ጋዝ፣ ውሃ፣ የቤት ስልክ (የሞባይል ስልክ ወይም የኬብል ሂሳቦች ብቻቸው ተቀባይነት የላቸውም)
  • ኢ-ቢል፣ የአመልካች ስም እና የአሁን አድራሻ ከሁለት ያሁኑ የፖስታ መልእክት ጋር ለሚያሳዩ የፍጆታ ዕቃዎች
  • ፍቃድ ባለው አካል የተረጋገጠ መግለጫ እና ሁለት የፖስታ እቃዎች
  • ከዲሲ የመንግስት ኤጀንሲ የሚላክ ሪፈራል
  • ከ 30 ቀናት ያልበለጡ በአመልካች የተቀበሉ ሥራ ላይ ያሉ የTANF፣ የምግብ ማህተም ወይም የMedicaid ጥቅማጥቅሞች ሰነዶች

ከሌላ ወላጅ የሚገኘውን ገቢ መረጃ መስጠት አለብኝ?
ባለሁለት ወላጅ ቤተሰብ ካለዎት፣ ከሁለቱም ወላጆች የገቢ መረጃን ማስገባት አለብዎት። ሌላው ወላጅ ከቤተሰቡ ከተለዩ፣ ነገር ግን የት እንዳሉየሚታወቅ ከሆነ፣ ሌላኛው ወላጅ ለቤተሰቡ የሚያደርጉትን አስተዋፅዖ ማስታወቂያ መስጠት አለባቸው። የሌላው ወላጅ የት እንዳለ የማይታወቅ ከሆነ፣ የገቢ መረጃቸው አያስፈልግም።

የልጅ እንክብካቤ ድጎማ ጥቅማጥቅሞች መፈቀዱን ለማወቅ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?
የልጅ እንክብካቤ ድጎማ ጥቅማጥቅሞች ሊፀድቁ የሚችሉበት በጣም ቅርብ የሆነ ቀን፣ ቃለ-መጠይቁን ያጠናቀቁበት እና ሁሉንም አስፈላጊ የሆኑ ማረጋገጫዎችን ያቀረቡበት ቀን ሲሆን፣ ይህም ልጅዎ እንዲሳተፍበት የሚፈልጉትን የልጅ እንክብካቤ አቅራቢ ስም ያካትታል።

ልጆቼን በተለያዩ አቅራቢዎች ጋ ማስመዝገብ እችላለሁ?
አዎ። ለልጆችዎ የተለያዩ ቦታዎችን ከመረጡ፣ የመቀበያ ሂደቱን በDHS ጋ በአካል ማጠናቀቅ አለብዎት። 

ድጎማ ካገኘሁ ለልጅ እንክብካቤ አገልግሎቶች ማንኛውም ወጪ ይኖር ይሆን?
ልጅዎ ለተመዘገበበት የልጅ እንክብካቤ አቅራቢ የጋራ ክፍያን በቀጥታ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ። የጋራ ክፍያው የልጅ እንክብካቤ ለሚያገኙ ሁለት ትልልቅ ልጆች ይሠራል። አገልግሎቶች ከጸደቀልዎት በኋላ ስለ እርስዎ የጋራ ክፍያ ወጪ እንዲያውቁ ይደረጋል።


Early Learning Services for Parents

Early Learning